መዝሙር 98:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእስራኤል ቤት ያለውን ጽኑ ፍቅርና ታማኝነት አስታወሰ፥ የምድር ዳርቻዎች ሁሉ የአምላካችንን ማዳን አዩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእስራኤል ቤት ምሕረቱን፣ ታማኝነቱንም ዐሰበ፤ የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ፣ የአምላካችንን ማዳን አዩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእስራኤል ሕዝብ የሰጠውን ፍቅርና ታማኝነት አስታውሶአል፤ በየስፍራው ያሉ ሕዝቦች ሁሉ የአምላካችንን ድል አድራጊነት አይተዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉ ታላቅ ስምህን ያመሰግናል፥ ግሩምና ቅዱስ ነውና። |
እርሱም፦ “የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሣ ከእስራኤልም የተረፉትን እንድትመልስ አገልጋዬ እንድትሆን እጅግ ቀላል ነገር ነውና ማዳኔ እስከ ምድር ዳር እንዲደርስ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ ይላል።
የምሥራች የሚናገር፥ ሰላምንም የሚያወራ፥ የመልካምንም ወሬ የምሥራች የሚናገር፥ መድኃኒትንም የሚያወራ፥ ጽዮንንም፦ አምላክሽ ነግሦአል የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ውብ ነው።
እኔም ለያዕቆብ የማልሁትን ቃል ኪዳኔን አስታውሳለሁ፤ እንዲሁም ለይስሐቅና ለአብርሃም የማልሁትንም ቃል ኪዳኔን አስታውሳለሁ፤ ምድሪቱንም አስታውሳለሁ።
“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።