Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 106:45 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

45 ለእነርሱም ኪዳኑን አሰበ፥ እንደ ጽኑ ፍቅሩም ብዛት ተጸጸተ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

45 ለእነርሱም ሲል ቃል ኪዳኑን ዐሰበ፤ እንደ ምሕረቱም ብዛት ከቍጣው ተመለሰ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

45 እነርሱን ለማዳን ቃል ኪዳኑን ያስታውስ ነበር፤ ስለ ታላቅ ፍቅሩም ምሕረት ያደርግላቸው ነበር።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 106:45
22 Referencias Cruzadas  

የጌታ መልአክ ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እጁን በዘረጋ ጊዜ፥ ጌታ ስለ ክፉው ነገር አዘነ፤ ሕዝቡን የሚቀሥፈውንም መልአክ “ይበቃል! እጅህን መልስ” አለው። በዚያን ጊዜ የጌታ መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።


እግዚአብሔር ግን በቸርነቱ ምሕረትን በማድረግ ረዳቸው እንጂ እንዲደመሰሱ አልፈቀደም፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የሰጠውን ቃል ኪዳን በማሰብ ሕዝቡን ስላልረሳው ነው።


ቃል ኪዳኑን ለዘለዓለም፥ እስከ ሺህ ትውልድ ያዘዘውን ቃሉን አሰበ፥


ጌታ ለሕዝቡ ይፈርዳልና፥ ባርያዎቹንም ይረዳልና።


እኛን በመዋረዳችን አስቦናልና፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥


ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።


የውኃው ማዕበል አያስጥመኝ፥ ጥልቁም አይዋጠኝ፥ ጉድጓድም አፉን በእኔ ላይ አይዝጋ።


አቤቱ፥ ተመለስ፥ እስከ መቼስ ነው? ለአገልጋዮችህ ራራ።


ጌታም በሕዝቡ ላይ አደርጋለሁ ያለውን ክፋ ነገር መለሰ።


ጌታ ስላደረገልን ሁሉ፥ የጌታን ቸርነትና የጌታን ምስጋና፥ እንደ ምሕረቱና እንደ ቸርነቱም ብዛት ለእስራኤል ቤት የሰጠውን የተትረፈረፈ ጽኑ ፍቅር እናገራለሁ።


ይህ ስለ እርሱ የተናገርሁበት ሕዝብ ከክፋቱ ቢመለስ፥ እኔ ላደርግበት ካሰብሁት ክፉ ነገር እጸጸታለሁ።


ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራልና፥


ነገር ግን በልጅነትሽ ወራት ከአንቺ ጋር የመሠረትኩትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፥ የዘለዓለምንም ቃል ኪዳን አቆማለሁ።


ኤፍሬም ሆይ! እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ! እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴትስ እንደ አድማህ አደርግሃለሁ? እንዴትስ እንደ ጲቦይም እመለከትሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተናውጣለች፥ ምሕረቴም ተነሣሥታለች።


እኔ አምላክ እንድሆናቸው አሕዛብ እያዩ ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው ከአባቶቻቸው ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን ስለ እነርሱ አስታውሳለሁ፤ እኔ ጌታ ነኝ።”


ጌታም ስለዚህ ነገር ተጸጸተ፤ “ይህ አይሆንም፥” ይላል ጌታ።


ጌታም ስለዚህ ነገር ተጸጸተ፤ “ይህ ደግሞ አይሆንም፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ጌታ ለሕዝቡ ይፈርዳል፥ ለአገልጋዮቹም ያዝናል። ኃይላቸውም እንደደከመ፥ የታሰረም ሆነ የተለቀቀ እንደሌለ ሲያዩ፥


ከዚያም በመካከላቸው ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወገዱ፤ ጌታንም አመለኩ፤ እርሱም የእስራኤልን መከራ ሊታገሠው የማይቻለው ሆነ።


ጌታ መሳፍንትን ባስነሣላቸው ጊዜ ከመስፍኑ ጋር ስለሚሆን፥ እርሱ በሕይወት እስካለ ድረስ ጌታ ከጠላቶቻቸው ያድናቸው ነበር፤ ከጠላቶቻቸው ሥቃይና መከራ ሲደርስባቸው በሚጮኹበት ጊዜ ጌታ ይራራላቸው ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos