ታጥለቀልቃቸዋለህ፥ እንደ ሕልም ናቸው፥ በማለዳም እንደሚያልፍ ሣር።
እንደ ጐርፍ ጠርገህ ስትወስዳቸው፣ እንደ ሕልም ይበንናሉ፤ እንደ ማለዳ ሣር ታድሰው ይበቅላሉ፤
ሕይወታችንን ልክ እንደ ሕልም ታሳልፈዋለህ፤ እኛ በየማለዳው እንደሚታደስ የሣር ቡቃያ ነን።
ከሌሊት ግርማ፥ በመዓልት ከሚበርር ፍላጻ፥
እንደ ሕልም ይበርራል፥ እርሱም አይገኝም፥ እንደ ሌሊትም ራእይ ይሰደዳል።
ጊዜያቸው ሳይደርስ ተነጠቁ፥ መሠረታቸውም እንደ ፈሳሽ ውኃ ፈሰሰ።”
በጥዋትና በማታ መካከል ይሰባበራሉ፥ ማንም ሳያስብ ለዘለዓለም ይጠፋሉ።
የደንገል ታንኳ እንደሚፈጥን፥ ንስርም ወደ ንጥቂያው እንደሚበርር ያልፋሉ።
ከሕልም እንደሚነቃ፥ አቤቱ፥ ስትነቃ መልካቸውን ትንቃለህ።
ማደሪያዬ ተነቀለች፥ እንደ እረኛ ድንኳንም ከእኔ ዘንድ ተወገደች፤ ሕይወቴንም እንደ ሸማኔ ጠቀለልኩት፤ እርሱም ከመጠቅለያው ይቈርጠኛል፤ ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ፍጻሜዬን አቀረብከው።
እስኪ ነጋ ድረስ ቈይቼ ነበር፤ እርሱ እንደ አንበሳ አጥንቴን ሁሉ ሰበረ፤ ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ፍጻሜዬን አቀረብከው።
አንድ ድምጽ “ጩኽ!” አለኝ፤ “ምን ብዬ ልጩኽ?” አልኩ። ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ምድረ በዳ አበባ ነው።
የጌታ እስትንፋስ ይነፍስበታል፤ ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፤ በእውነት ሕዝቡ ሣር ነው።
ምክንያቱም፥ “ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤