መዝሙር 9:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጽዮን ለሚኖር ለጌታ ዘምሩ፥ በአሕዛብም መካከል ድንቅ ሥራውን ንገሩ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደም ተበቃዩ ዐስቧቸዋልና፤ የጭቍኖችንም ጩኸት አልዘነጋም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የተጨቈኑትን ያስታውሳል ጩኸታቸውን አይረሳም የሚበድሉአቸውንም ይቀጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደማቸውን የሚመራመር እርሱ አስቦአልና፥ የድሆችንም ጩኸት አልረሳምና። |
በተለይም ምናሴ የንጹሓን ሰዎችን ደም በማፍሰሱና ኢየሩሳሌምንም በንጹሓን ደም በመሙላቱ ምክንያት ይህ ሁሉ ሊፈጸም ችሎአል፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ለምናሴ ምሕረት ሊያደርግለት አልፈቀደም።
አየኸው፥ አንተ ክፋትንና ቁጣን ትመለከታለህና በእጅህ ፍዳውን ለመስጠት፥ ምስኪን እራሱን ለአንተ አሳልፎ ይሰጣል፥ ለድሀ አደግም ረዳቱ አንተ ነህ።
ጌታም አለ፦ “በግብጽ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፥ በአስገባሪዎቻቸውም ምክንያት የሚጮሁትን ጩኸት ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ።
በምድር በሚኖሩት ላይ በበደላቸው ምክንያት ቁጣውን ሊያመጣባቸው፥ እነሆ፥ ጌታ ከስፍራው ይወጣል፤ ምድርም ያፈሰሰችውን ደም ትገልጣለች፥ የተገደሉትንም ከእንግዲህ ወዲህ አትሸሽግም።
በዚህም ምክንያት ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው ጻድቅ ደም ሁሉ በእናንተ ላይ ይደርሳል።