መዝሙር 84:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው፥ ለዓለምና ለዘለዓለምም ያመሰግኑሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብፁዓን ናቸው፤ አንተን ብርታታቸው ያደረጉ፣ በልባቸው የጽዮንን መንገድ የሚያስቡ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ጽዮን ተራራ መንፈሳዊ ጒዞ ለማድረግ የሚፈልጉና የአንተን ርዳታ የሚያገኙ እንዴት የተባረኩ ናቸው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለዘለዓለም አትቈጣን፥ ቍጣህንም ለልጅ ልጅ አታስረዝም። |
ፍርድህን በምድር ላይ በፈረድክ ጊዜ በዓለም የሚኖሩ ጽድቅን ይማራሉና ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፥ መንፈሴም በውስጤ ወደ አንተ ትገሠግሣለች።
ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የማደርገው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።
ብዙዎች አሕዛብ መጥተው፦ ኑ ወደ ጌታ ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ እኛም በፍለጋው እንሄዳለን ይላሉ፤ ከጽዮን ሕግ፥ ከኢየሩሳሌምም የጌታ ቃል ይወጣልና።
እርሱ ግን፥ “ጸጋዬ ይበቃሃል፤ ኀይሌ በድካም ፍጹም ይሆናል” አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል እንዲያድርብኝ በበለጠ ደስታ በድካሜ መመካትን እወዳለሁ።