አቤቱ፥ ውኆች አዩህ፥ ውኆችም አይተውህ ፈሩ፥ ጥልቆችም ተነዋወጡ።
ደመናት ውሃን አንጠባጠቡ፤ ሰማያት አንጐደጐዱ፤ ፍላጾችህም ዙሪያውን አብለጨለጩ።
ደመናዎች ዝናብን አዘነቡ፤ ነጐድጓድ በሰማይ አስገመገመ፤ የመብረቅ ፍላጻዎችህም ከላይ ከሰማይ አንጸባረቁ።
ነገር ግን እርሱን መበደልን እንደገና ደገሙ፥ ልዑልንም በምድረ በዳ አስመረሩት።
ፍላጻውን ሰደደ፤ በተናቸውም፤ በመብረቁም ብልጭታ አወካቸው።
ባሕር አየች፥ ሸሸችም፥ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ።
መብረቆችህን ብልጭ አድርጋቸው በትናቸውም፥ ፍላጾችህን ላካቸው አስደንግጣቸውም።
ጌታ ከሰማያት አንጐደጐደ፥ ልዑልም ቃሉን ሰጠ። በረዶና የእሳት ፍምም፤
የምድር ነገሥታት፥ ለእግዚአብሔር ተቀኙ፥ ለጌታም ዘምሩ።
ተራሮች አንተን አይተው ተወራጩ፥ የውኃ ወጀብ አለፈ፥ ጥልቁም ድምፁን ሰጠ፥ እጁንም ወደ ላይ አነሳ።
በቀስቶችህ ብርሃን፥ በጦርህ መብረቅ ፀዳል፥ ፀሐይና ጨረቃ በመኖሪያቸው ቀጥ ብለው ቆሙ።
አቤቱ፥ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፥ ከኤዶምያስም ሜዳ በተራመድህ ጊዜ፥ ምድሪቱ ተናወጠች፥ ሰማያቱም አንጠበጠቡ፥ ደመናትም ደግሞ ውኃን አንጠበጠቡ።