La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 75:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ ወይም ከምድረበዳ የለምና፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን የሚፈርድ እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ አንዱን ዝቅ፣ ሌላውን ከፍ ያደርጋል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በአንዱ ላይ የሚፈርድ፥ ሌላውን ነጻ የሚያወጣ፥ ትክክለኛ ፈራጅ እግዚአብሔር ነው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አንተ ግን፥ ግሩም ነህ፤ ቍጣ​ህን ማን ይቃ​ወ​ማል?

Ver Capítulo



መዝሙር 75:7
19 Referencias Cruzadas  

እንደ ትላንትና እንዳለፉት ሦስት ቀናት ሳኦል በእኛ ላይ ነግሦ በነበረ ጊዜ፥ እስራኤልን በጦርነት የምትመራቸው አንተ ነበርህ፤ ጌታም፥ ‘ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፤ መሪያቸውም ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር።”


ዳዊትም ሜልኮልን እንዲህ አላት፤ “አዎን ያሸበሸብኩት በጌታ ፊት ነው፤ በአባትሽና በቤቱ ካሉት ሁሉ አስበልጦ በጌታ ሕዝብ በእስራኤል ላይ ገዥ አድርጎ በመረጠኝ በጌታ ፊት አሁንም እጨፍራለሁ።


ጌታ የተዋረዱትን ያነሣል፥ ክፉዎችን ግን እስከ ምድር ድረስ ያዋርዳል።


ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ፥ እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና።


ጻድቅ በቀልን ባየ ጊዜ ደስ ይለዋል፥ በክፉዉም ደም እግሮቹን ይታጠባል።


ገዥዎችን ከዙፋናቸው አውርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤


እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንደሚሰጣችሁ፥ እንድትሄዱና ፍሬ እንድታፈሩ ፍሬአችሁም እንዲኖር ሾምኋችሁ።


የእነርሱ መጣል ለዓለም እርቅን ካስገኘ፥ ተቀባይነት ማግኘታቸውማ ከሞት መነሣት ነው ከማለት በቀር ምን መሆን ይችላል?


ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር በወደደ ጊዜ፥


ዐመፅ እንደ ሟርተኛነት ያለ ኃጢአት፥ እልኸኝነትም እንደ ጣዖት አምልኮ ያለ ክፉ ነገር ነው፤ አንተ የጌታን ቃል ንቀሃልና እርሱም ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል።”


ሳሙኤልም እንዲህ አለው፤ “ጌታ የእስራኤልን መንግሥት ዛሬ ከአንተ ቀዶታል፤ ከአንተም ለሚሻል ለጎረቤትህ አሳልፎ ሰጥቶታል።


ጌታ ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? ወደ ቤተልሔሙ ሰው ወደ እሴይ ስለምልክህ፥ ዘይት በቀንድ ሞልተህ ሂድ፤ ከልጆቹ አንዱ ንጉሥ ይሆን ዘንድ መርጬዋለሁ” አለው።