La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 57:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ልቤ ጽኑ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጽኑ ነው፥ እቀኛለሁ፥ እዘምራለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነፍሴ ሆይ፤ ንቂ! በገናና መሰንቆም ተነሡ! እኔም ማልጄ እነሣለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነፍሴ ሆይ! ተነሺ፤ በገናዬና መሰንቆዬም ተነሡ! እኔም በማለዳ እነሣለሁ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ደ​ሚ​ቀ​ልጥ ሰም ያል​ቃሉ፤ እሳት ወደ​ቀች፥ ፀሐ​ይ​ንም አላ​የ​ኋ​ትም።

Ver Capítulo



መዝሙር 57:8
11 Referencias Cruzadas  

በበገናና በመሰንቆ በመለከትም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ጌታ ቤት ገቡ።


በመለከት ድምፅ አወድሱት፥ በበገናና በመሰንቆ አወድሱት።


ስለዚህ ልቤን ደስ አለው ነፍሴም ሐሴት አደረገች፥ ሥጋዬም ደግሞ በተስፋ ታድራለች፥


እነሆ፥ አሁን በዙሪያ ባሉ በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ፥ በድንኳኑም የእልልታ መሥዋዕትን ሠዋሁ፥ ለጌታ እቀኛለሁ እዘምርለትማለሁ።


ልቅሶዬን ወደ እልልታ ለወጥህልኝ፥ ማቄን ቀድደህ ደስታንም አስታጠቅኸኝ።


ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ፥ ጉልማስነቴንም ደስ ወዳሰኛት ወደ አምላኬ እገባለሁ፥ አቤቱ አምላኬ፥ በበገና አመሰግንሃለሁ።


ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፥ ኃይልሽን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ አይገባብሽምና ጌጠኛ ልብስሽን ልበሺ።


እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች ሆይ፥ ጌታ ሕዝቡን አጽናንቶአልና፥ ኢየሩሳሌምንም ታድጎአልና ደስ ይበላችሁ፥ በአንድነትም ዘምሩ።


ስለዚህ ልቤን ደስ አለው፤ ልሳኔም ሐሤት አደረገ፤ ደግሞም ሥጋዬ በተስፋ ያድራል፤


ንቂ፥ ንቂ፥ ዲቦራ ሆይ፥ ንቂ፥ ንቂ፥ ቅኔውን ተቀኚ፥ ባራቅ ሆይ፥ ተነሣ፥ የአቢኒኤም ልጅ ሆይ፥ ምርኮህን ማርክ።