La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 55:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ልቤ በላዬ ተናወጠብኝ፥ የሞት ድንጋጤም ወደቀብኝ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ፍርሀትና እንቅጥቃጤ መጣብኝ፤ ሽብርም ዋጠኝ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ፍርሀትና ድንጋጤ ይዞኛል፤ መላ ሰውነቴም ተሸብሮአል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሁል​ጊዜ ቃሎ​ችን ይጸ​የ​ፉ​ብ​ኛል፤ በእኔ ላይም የሚ​መ​ክ​ሩት ሁሉ ለክፉ ነው።

Ver Capítulo



መዝሙር 55:5
12 Referencias Cruzadas  

ከዚያም ዳዊት በኢየሩሳሌም ላሉት አገልጋዮቹ ሁሉ፥ “ተነሡ እንሽሽ፤ ያለበለዚያ ከአቤሴሎም እጅ ማምለጥ አንችልም፤ ፈጥኖ እንዳይዘን፥ ክፉም እንዳያመጣብን፤ ከተማዪቱንም በሰይፍ ስለት እንዳይመታ ፈጥናችሁ እንሂድ” አላቸው።


እኔ ባሰብሁ ቍጥር እደነግጣለሁ፥ ሰውነቴንም መንቀጥቀጥ ይይዘዋል።


ሁሉን የሚችል የአምላክ ፍላጻ በሥጋዬ ውስጥ ነው፥ መርዙንም ነፍሴ ትጠጣለች፥ የእግዚአብሔር ሽብሮች በኔ ላይ ተሰልፈዋል።


ሥጋዬ አንተን ከመፍራት የተነሣ ደነገጠ፥ ከፍርድህ የተነሣ ፈርቻለሁ።


የሲኦል ገመዶች ተበተቡኝ፥ የሞት ወጥመዶችም ደረሱብኝ።


ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።


አምላክ ሆይ፥ ጩኸቴን ስማ፥ ጸሎቴንም አድምጥ።


ልቤ ራደ፥ ድንጋጤ አስደመመኝ፥ ተስፋ ያደረግሁትም ድንግዝግዝታ ፍርሃት አሳደረብኝ።


ማቅ ይለብሳሉ፥ ድንጋጤም ይሸፍናቸዋል፥ በሁሉም ፊቶች ላይ እፍረት ይሆናል፥ ራሳቸውም ሁሉ መላጣ ይሆናል።


በስቃይ ጣር ውስጥ ሆኖ በብርቱ ይጸልይ ነበር፤ ላቡም ወደ መሬት እንደሚንጠባጠቡ የደም ጠብታዎች ሆኑ።