አሕዛብ ሁላችሁ፥ ይህን ስሙ፥ በዓለም የምትኖሩትም ሁላችሁ፥ አድምጡ፥
ዝቅተኞችና ከፍተኞች፣ ባለጠጎችና ድኾች ይህን በአንድነት ስሙ።
ከፍተኞችና ዝቅተኞች፥ ሀብታሞችና ድኾች ስሙ፤
ከክብሩ ውበት ከጽዮንም፥
እነርሱ ሁሉ የእጁ ሥራ ናቸውና ለአለቆች አያደላም፥ ሀብታሙንም ሰው ከድሀው ይበልጥ አይመለከትም።
ሕዝቦች ሆይ፥ ሁልጊዜ በእርሱ ታመኑ፥ ልባችሁንም በፊቱ አፍስሱ፥ እግዚአብሔር መጠጊያችን ነው።
ሀብታምና ድሀ ይገናኛሉ፥ ሁለቱንም የፈጠራቸው ጌታ ነው።
እናንተ አሕዛብ ሆይ፥ ቅረቡ፥ ስሙ፤ እናንተ ወገኖች ሆይ፥ አድምጡ፤ ምድርና ሞላዋ፥ ዓለምና ከእርሷ የሚወጣ ሁሉ ይስሙ።
ሕዝቦች ሆይ! ሁላችሁም ስሙ፤ ምድርና ሞላዋ ታድምጥ፤ ጌታ በቅዱስ መቅደሱ ሆኖ፥ ጌታ አምላክ በእናንተ ላይ ይመስክርባችሁ።