ብዙ መሬት በስማችው ቢያስጠሩም እንኳን፥ መቃብራቸው የዘለዓለም ቤታቸው፥ ለልጅ ልጅ የሚሆን ማደሪያቸውም ነው።
ሰው በሀብቱ እንደ ተከበረ አይዘልቅም፤ ታይተው የሚጠፉ እንስሳትን ይመስላል።
ሰው ምንም ሀብታም ቢሆን ዘለቄታ የለውም፤ እንደ እንስሶች ይሞታል።
ብራብም አልለምንህም፥ ዓለም ሁሉ በመላው የእኔ ነውና።
ቃየንም ሚስቱን አወቀ፥ ፀነሰችም፥ ሔኖክንም ወለደች፤ ከተማም መሠረተ፤ ከተማይቱንም በልጁም ስም “ሔኖክ” ብሎ ጠራት።
አቤቱ፥ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ፥ የዘመኔ ቁጥሮች ምን ያህል እንደ ሆኑ፥ እኔ ምን ያህል ረጋፊ እንደሆንኩ አውቅ ዘንድ።
ሆኖም ወደ አባቶቹ ትውልድ ይወርዳል፥ ለዘለዓለም ብርሃንን ወደ ማያዩበት።
ነገር ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፥ ከአለቆችም እንደ አንዱ ትወድቃላችሁ።
ሰውም ጊዜውን አያውቅም፥ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ።
ምክንያቱም፥ “ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤