መዝሙር 48:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላክ ሆይ፥ በመቅደስህ ውሰጥ ርኅራኄህን አሰላሰልን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ ሆይ፤ ምስጋናህ እንደ ስምህ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ይዘልቃል፤ ቀኝ እጅህም ጽድቅን የተሞላች ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ምስጋናህ እስከ ዓለም ዳርቻ እንደ ደረሰ ስምህም እንደዚሁ ገናና ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠቢባንን ሲሞቱ ባየሃቸው ጊዜ፥ እንደዚሁ ልብ የሌላቸው ሰነፎች ይጠፋሉ፥ ገንዘባቸውንም ለሌሎች ይተዋሉ። |
“ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በሕዝቦች መካከል ታላቅ ይሆናል፤ በሁሉም ስፍራ ለስሜ ዕጣን ያመጣሉ፥ ንጹሕ ቁርባንም ያቀርባሉ፤ ስሜ በሕዝቦች መካከል ታላቅ ይሆናል፥” ይላል የሠራዊት ጌታ።
“በመንጋው ውስጥ ተባዕት እያለው ለጌታ ተስሎት እያለ ነውር ያለበትን የሚሠዋ ተንኮለኛ ሰው የተረገመ ነው። እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፥ “ስሜም በሕዝቦች መካከል የተፈራ ነውና።”