Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 48:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 አምላክ ሆይ፤ ምስጋናህ እንደ ስምህ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ይዘልቃል፤ ቀኝ እጅህም ጽድቅን የተሞላች ናት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አምላክ ሆይ፥ በመቅደስህ ውሰጥ ርኅራኄህን አሰላሰልን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 አምላክ ሆይ! ምስጋናህ እስከ ዓለም ዳርቻ እንደ ደረሰ ስምህም እንደዚሁ ገናና ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ጠቢ​ባ​ንን ሲሞቱ ባየ​ሃ​ቸው ጊዜ፥ እን​ደ​ዚሁ ልብ የሌ​ላ​ቸው ሰነ​ፎች ይጠ​ፋሉ፥ ገን​ዘ​ባ​ቸ​ው​ንም ለሌ​ሎች ይተ​ዋሉ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 48:10
16 Referencias Cruzadas  

“ከፀሓይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ፣ ስሜ በሕዝቦች መካከል የከበረ ይሆናል፤ በየስፍራውም ሁሉ ለስሜ ዕጣንና ንጹሕ ቍርባን ያቀርባሉ፤ ስሜ በሕዝቦች መካከል የከበረ ይሆናልና” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ድረስ፣ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን።


በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የዚህን ሕግ ቃሎች በጥንቃቄ ባትከተልና አስደናቂና አስፈሪ የሆነውን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ስም ባታከብር፣


ከነዓናውያንና ሌሎቹ የምድሪቱ ነዋሪዎች ሁሉ ይህን ሲሰሙ ይከብቡናል፤ ስማችንንም ከምድር ገጽ ያጠፉታል፤ እንግዲህ ስለ ታላቁ ስምህ ስትል የምታደርገው ምንድን ነው?”


እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ። አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ።


ከዚያም ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆ አንድ ነጭ ፈረስ ነበረ፤ በፈረሱም ላይ፣ “ታማኝና እውነተኛ” የሚባል ተቀምጦ ነበር፤ እርሱም በጽድቅ ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።


ፍርዱ እውነትና ጽድቅ ነውና፤ በዝሙቷ ምድርን ያረከሰችውን፣ ታላቂቱን አመንዝራ ፈርዶባታል፤ ስለ ባሮቹም ደም ተበቅሏታል።”


“በመንጋው ውስጥ ተቀባይነት ያለው ተባዕት በግ ኖሮት ይህንኑ ሊሰጥ ተስሎ ሳለ፣ በማታለል ነውር ያለበትን እንስሳ ለጌታ የሚሠዋ ርጉም ይሁን፤ እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝ፤ ስሜም በሕዝቦች ዘንድ ሊፈራ የሚገባ ነውና” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ፣ በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።


ፍትሕን የምትወድድ፣ ኀያል ንጉሥ ሆይ፤ አንተ ትክክለኝነትን መሠረትህ፤ ፍትሕንና ቅንነትንም፣ ለያዕቆብ አደረግህ።


ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃን ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ፣ ከጓደኞችህ ይልቅ አንተን የደስታ ዘይት ቀባህ።


እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፤ የጽድቅ ሥራም ይወድዳል፤ ቅኖችም ፊቱን ያያሉ።


እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ፍርዱም በምድር ሁሉ ላይ ነው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios