መዝሙር 45:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ፥ በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስምሽን በትውልድ ሁሉ ዘንድ መታሰቢያ አደርጋለሁ፤ ስለዚህ ሕዝቦች ከዘላለም እስከ ዘላለም ያወድሱሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ በየትውልዱ ዝናህን እገልጣለሁ፤ ስለዚህ ሕዝቦች ሁሉ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ያመሰግኑሃል። |
ርግቤ፥ የእኔ እንከን የለሽ አንዲት ናት፥ ለእናትዋ አንዲት ለወለደቻትም የተመረጠች ናት። ቈነጃጅትም አይተው ብፅዕት አሉአት፥ ንግሥቶችና ቁባቶችም አመሰገኑአት።
ከእነርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በአንተ ላይ ያለው መንፈሴ በአፍህም ውስጥ ያደረግሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ ከአፍህ፥ ከዘርህም አፍ፥ ከዘር ዘርህም አፍ አይለይም፥ ይላል ጌታ።
“ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በሕዝቦች መካከል ታላቅ ይሆናል፤ በሁሉም ስፍራ ለስሜ ዕጣን ያመጣሉ፥ ንጹሕ ቁርባንም ያቀርባሉ፤ ስሜ በሕዝቦች መካከል ታላቅ ይሆናል፥” ይላል የሠራዊት ጌታ።