ማሕልየ መሓልይ 6:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ርግቤ፥ የእኔ እንከን የለሽ አንዲት ናት፥ ለእናትዋ አንዲት ለወለደቻትም የተመረጠች ናት። ቈነጃጅትም አይተው ብፅዕት አሉአት፥ ንግሥቶችና ቁባቶችም አመሰገኑአት። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 እንከን የሌለባት ርግቤ ግን ልዩ ናት፤ እርሷ ለወለደቻት የተመረጠች፣ ለእናቷም አንዲት ናት፤ ቈነጃጅት አይተው “የተባረክሽ ነሽ” አሏት፤ ንግሥቶችና ቁባቶችም አመሰገኗት። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 እኔ ግን የምወደው አንዲትዋን ብቻ ነው፤ እርስዋም ምንም እንከን የሌለባት እንደ ርግብ የተዋበች ናት፤ እርስዋ ለእናትዋ አንድ ናት፤ የወለደቻት እናትዋም ከሁሉ አብልጣ ታፈቅራታለች፤ ቈነጃጅትም እርስዋን እየተመለከቱ ያወድሱአታል፤ ነገሥታትና የንጉሥ ቊባቶች ያሞግሡአታል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ርግቤ መደምደሚያዬም አንዲት ናት፤ ለእናቷ አንዲት ናት፥ ለወለደቻትም የተመረጠች ናት። ቈነጃጅትም አይተው አሞገሱአት፥ ንግሥታትና ቁባቶችም አመሰገኑአት። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ርግቤ መደምደሚያዬም አንዲት ናት፥ ለእናትዋ አንዲት ናት ለወለደቻትም የተመረጠች ናት። ቈነጃጅትም አይተው አሞገሱአት፥ ንግሥታትና ቍባቶችም አመሰገኑአት። Ver Capítulo |