እኔስ፦ “አቤቱ፥ ማረኝ፥ አንተን በድያለሁና ነፍሴን ፈውሳት” አልሁ።
ጠላቶቼ በክፋት በመናገር፣ “የሚሞተው መቼ ነው? ስሙስ የሚደመሰሰው ምን ቀን ነው?” ይላሉ።
ጠላቶቼ ብዙ ክፉ ነገር በእኔ ላይ በመናገር “መቼ ይሞታል? መቼስ ስሙ ተረስቶ ይቀራል?” ይላሉ።
ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኀኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።
መታሰቢያው ከምድር ላይ ይጠፋል፥ በሜዳም ስም አይቀርለትም።
እንደ ፋንድያ ለዘለዓለም ይጠፋል፥ ያዩትም፦ ወዴት ነው ያለው? ይላሉ።
ነቅቼ፥ በሰገነትም እንደሚኖር ብቸኛ ድንቢጥ ሆንሁ።
ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ከቁስሌ ገለል ብለው ቆሙ፥ ዘመዶቼም ርቀው ቆሙ።
አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፥ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ።
አንተን ብቻ በደልሁ፥ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ፥ በነገርህ ትጸድቅ ዘንድ በፍርድህም ንጹሕ ትሆን ዘንድ።
አቤቱ፥ ሰው ረግጦኛልና ማረኝ፥ ሁልጊዜም ተዋጊ አስጨንቆኛል።
ማረኝ፥ አቤቱ፥ ማረኝ፥ ነፍሴ አንተን ታምናለችና፥ ጉዳት እስኪያልፍ ድረስ በክንፎችህ ጥላ እታመናለሁ።
እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም፥ ፊቱንም በላያችን ያብራ፥
ወደ እኔ ተመልከት፥ ራራልኝ፥ ኃይልህን ለአገልጋይህ፥ ማዳንህንም ለአግልጋይቱ ልጅ ለእኔ ስጥ።
አቤቱ፥ ቀኑን ሁሉ ወደ አንተ እጮኻለሁና ማረኝ።
የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው፥ የክፉ ስም ግን ይጠፋል።