ለሰንበት መታሰቢያ፥ የዳዊት መዝሙር።
እግዚአብሔር ሆይ፤ በቍጣህ አትገሥጸኝ፤ በመዓትህም አትቅጣኝ።
እግዚአብሔር ሆይ! በቊጣህ አትገሥጸኝ፤ በኀይለኛ ቊጣህም አትቅጣኝ።
“በአንደበቴ እንዳልስት አፌን እጠብቃለሁ፤ ኃጥኣን በፊቴ በተቃወሙኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ” አልሁ፤
ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች ስለ ስምንተኛ፥ የዳዊት መዝሙር።
ለመዘምራን አለቃ፥ ለመታሰቢያ፥ የዳዊት መዝሙር።
በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ፥ በታችኛው ጉድጓድ አስቀመጥኸኝ።
የምሥራቅ ነፋስ እንደሚነፍስበት ቀን በጠንካራ ዐውሎ አስወገዳቸው፤ በጦርነት ሰደዳቸው፥ ቀሰፋቸውም።
በጥቂት ቁጣ ለቅጽበተ ዐይን ፊቴን ከአንቺ ሰወርሁ፥ በዘለዓለምም ቸርነት እምርሻለሁ፥ ይላል ታዳጊሽ ጌታ።
አቤቱ! ገሥጸኝ፤ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቁጣ አይሁን።
አንተን ለማዳን ከአንተ ጋር ነኝና፥ ይላል ጌታ፤ አንተንም የበተንሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ እንደጥፋትህ መጠን እቀጣሃለሁ እንጂ ያለ ቅጣት ከቶ አልተውህም።
ጌታ ሆይ፥ ዝናህን ሰምቻለሁ፥ በሥራህም ጌታ ሆይ ፈራሁ፥ በዓመታት መካከል አድሰው፥ በዓመታት መካከል አስታውቀው፥ በቁጣ ጊዜ ምሕረትን አስብ።
እግዚአብሔር ሊያጠፋችሁ በመነሳቱ ከቁጣውና ከመዓቱ የተነሣ ፈራሁ። ጌታ ግን ልመናዬን ደግሞ ሰማኝ።