መዝሙር 23:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፥ በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብሄድ እንኳ፣ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንህ፣ ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ፣ እነርሱ ያጽናኑኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጣም ጨለማ በሆነ ሸለቆ በኩል ባልሄድም እንኳ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንክ፥ ምንም ክፉ ነገር አልፈራም። ያንተ በትርና ምርኲዝ ያጽናኑኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልቡ ንጹሕ የሆነ፥ እጆቹም የነጹ፥ በነፍሱ ላይ ከንቱን ያልወሰደ፥ ለባልንጀራውም በሽንገላ ያልማለ። |
እነርሱም፦ ‘ከግብጽ ምድር ያወጣን፥ በምድረ በዳም በባድማ ጉድጓድም ባለበት ምድር፥ በውኃ ጥምና በሞት ጥላ ምድር፥ ማንም በማያልፍበትና ማንም በማይቀመጥበት ምድር የመራን ጌታ ወዴት አለ?’ አላሉም።
በአትክልት ቦታ መካከል ባለው ጥሻ ብቻቸውን የተቀመጡት የርስትህን መንጋ፥ ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፤ እንደ ቀደመው ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።
የሠራዊት ጌታም እንዲህ ይላል፦ በዚያ ዘመን ከሁሉም የአሕዛብ ቋንቋ ዐሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው፦ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና እኛም ከእናንተ ጋር እንሂድ” ይላሉ።
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” ትርጉሙም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” ማለት ነው።