ሃሌ ሉያ። ጌታን በመቅደሱ አወድሱት፥ በኃይሉ ጠፈር አወድሱት።
ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት፤ በታላቅ ጠፈሩ አመስግኑት።
እግዚአብሔርን አመስግኑ! እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት! የሚያስደንቅ ኀይሉ ባለበት በሰማይ አመስግኑት!
እግዚአብሔርን በተቀደሱ ቦታዎች አመስግኑት፤ በኀይሉ ጽናት አመስግኑት።
ይህ ለሚመጣ ትውልድ ይጻፍ፥ የሚፈጠርም ሕዝብ ለጌታ እልል ይላል፥
በሌሊት በቤተ መቅደስ ውስጥ እጆቻችሁን አንሡ፥ ጌታንም ባርኩ።
ሃሌ ሉያ። ለጌታ አዲሱን ቅኔ ተቀኙለት፥ ውዳሴው በቅዱሳኑ ጉባኤ ነው።
ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ ጠፈርም የእጁን ሥራ ያወራል።
የጌታ ድምፅ ዋላዎችን ያጠነክራቸዋል፥ ጫካዎቹንም ይገልጣል፥ ሁሉም በመቅደሱ፦ ምስጋና ይላል።
እኔም አየሁ፥ እነሆ ከኪሩቤል ራስ በላይ ካለው ጠፈር ከፍ ብሎ እንደ ሰንፔር ድንጋይ ያለ፥ ዙፋን የሚመስል ነገር ታየ።