መዝሙር 149:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሃሌ ሉያ። ለጌታ አዲሱን ቅኔ ተቀኙለት፥ ውዳሴው በቅዱሳኑ ጉባኤ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሃሌ ሉያ። ለእግዚአብሔር አዲስ ቅኔ ተቀኙ፤ ምስጋናውንም በቅዱሳን ጉባኤ ዘምሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን አመስግኑ! ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩ! በምእመናን ጉባኤ አመስግኑት! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን አዲስ ምስጋናን አመስግኑት፤ ምስጋናውም በጻድቃኑ ጉባኤ ነው። |
ወደ ባሕር የምትወርዱ በእርሷም ውስጥ ያላችሁ ሁሉ፥ ደሴቶችና በእነርሱም ላይ የምትኖሩ፥ ለጌታ አዲስ መዝሙር፥ ከምድርም ዳርቻ ምስጋናውን ዘምሩ።
“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።