በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ጌታን አመሰግናለሁ፥ በምኖርበት ዘመን ሁሉ ለአምላኬ እዘምራለሁ።
በምኖርበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ በሕይወትም እስካለሁ ለአምላኬ እዘምራለሁ።
በሕይወቴ ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ በምኖርበት ዘመን ሁሉ ለአምላኬ እዘምራለሁ።
እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ይሠራታል፥ ከእስራኤልም የተበተኑትን ይሰበስባል።
በሕይወቴ ሳለሁ ለጌታ እቀኛለሁ፥ ለአምላኬም በምኖርበት ዘመን ሁሉ እዘምራለሁ።
ቸርነትህ ከሕይወት ይሻላልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።
ነገሥታት ሆይ፥ ስሙ፥ መኳንንት ሆይ፥ አድምጡ፥ እኔ ለጌታ እቀኛለሁ፥ ለእስራኤል አምላክ ለጌታ እዘምራለሁ።