አድነኝ፥ አፋቸውም ምናምንን ከሚናገር፥ ቀኛቸውም የሐሰት ቀኝ ከሆነ፥ ከባዕድ ልጆች እጅ አስጥለኝ።
አንደበታቸው ሐሰትን ከሚናገር፣ ቀኝ እጃቸው የቅጥፈት ቀኝ እጅ ከሆነችው፣ ከባዕዳን እጅ ታደገኝ፤ አድነኝም።
ከባዕዳን ጠላቶች እጅ ታድገህ አድነኝ፤ አፋቸው ሐሰትን ይናገራል፤ ቀኝ እጃቸውም ለሐሰት መሐላ ይነሣል።
“ለመንግሥትህ ክብር ይገባል” ይላሉ፥ ኀይልህንም ይነጋገራሉ፥
አቤቱ፥ አድነኝ፥ ደግ ሰው አልቆአልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና።
አመድ ይበላል፥ የተታለለ ልብ አስቶታል፥ ነፍሱን ለማዳን አይችልም፥ ወይም፦ “በቀኝ እጄ ሐሰት አለ?” ብሎም አይጠይቅም።