የጌታን ዝማሬ በባዕድ ምድር እንዴት እንዘምራለን?
የእግዚአብሔርን ዝማሬ፣ እንዴት በባዕድ ምድር እንዘምር!
ለእግዚአብሔር መቅረብ የሚገባውን መዝሙር በባዕድ አገር እንዴት እንዘምራለን?
አቤቱ፥ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያመሰግኑሃል፤ የአፍህን ቃል ሁሉ ሰምተዋልና።
ለማልቀስ ጊዜ አለው፥ ለመሳቅም ጊዜ አለው፥ ዋይ ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመዝፈንም ጊዜ አለው፥
በዚያም ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወደ ልቅሶና ወደ ዋይታ፥ ጠጉራችሁን ወደ መንጨትና ማቅንም ወደ መልበስ ጠራችሁ።
አንቺም በልብሽ፦ “የወላድ መካን ሆኛለሁና፥ እኔም ብቻዬን ተሰድጄአለሁ፥ ተቅበዝብዤአለሁ፥ እነዚህን ማን ወለደልኝ? እነዚህንስ ማን አሳደጋቸው? እነሆ፥ ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤ እነዚህስ ወዴት ነበሩ?” ትያለሽ።
ለጌታም የወይን ጠጅን ቁርባን አያፈስሱም፥ መሥዋዕታቸውም ደስ አያሰኘውም፤ እንደ ኀዘን እንጀራም ይሆንባቸዋል፥ የሚበሉትም ሁሉ ይረክሳሉ፤ እንጀራቸውም ለሆዳቸው ይሆናል እንጂ ወደ ጌታ ቤት አይገባም።
በዚያ ቀን የመቅደሱ ዝማሬ ዋይታ ይሆናል፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ “የሰዎችም ሬሳ ይበዛል፥ በየስፍራውም ሁሉ በዝምታ ይጣላል።”