በዚያን ጊዜ የጐርፍ ውኃ በነፍሳችን ላይ ባለፈ ነበር።
ደራሽ ውሃም ጠራርጎ በወሰደን ነበር።
ብርቱ ማዕበልም ባሰጠመን ነበር።”
ወደ ጠማማነት የሚመለሱትን ግን ዐመፃን ከሚሠሩት ጋር እግዚአብሔር ይወስዳቸዋል። ሰላም በእስራኤል ላይ ይሁን።
እስከዚህ ድረስ ድረሺ፥ አትለፊ፥ በዚህም ለትዕቢተኛው ማዕበልሽ ገደብ ይሁን አልሁ።
በውኑ እኔን አትፈሩምን? ይላል ጌታ፤ ከፊቴስ አትደነግጡምን? አልፎት እንዳይሻገር አሸዋን በዘለዓለም ትእዛዝ ለባሕር ድንበር አድርጌአለሁ፤ ሞገዱም ቢናወጥ አያሸንፍም፥ ቢጮኽም አያልፈውም።