La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 116:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አቤቱ፥ እኔ አገልጋይህ ነኝ፥ አገልጋይህ፥ የሴት አገልጋይህም ልጅ ነኝ፤ ሰንሰለቴን ሰበርህ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ በእውነት ባሪያህ ነኝ፤ እኔ የሴት ባሪያህ ልጅ፣ ባሪያህ ነኝ፤ ከእስራቴም ፈታኸኝ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ሆይ! እኔ የአንተ ነኝ፤ የብላቴናይቱ አገልጋይህ ልጅ ነኝ፤ እስራቴን ፈተህልኛል። ከሞት ያዳንከኝ አንተ ነህ።

Ver Capítulo



መዝሙር 116:16
11 Referencias Cruzadas  

አቤቱ፥ ስለ ባርያህ ስትል እንደ ልብህ ይህን ታላቅ ነገር ሁሉ በማስታወቅ ይህን ተአምራት ሁሉ አድርገሃል።


እኔ ባርያህ ነኝ፥ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ምስክርህንም አውቃለሁ።


በጽኑ ፍቅርህ ጠላቶቼን ደምስሳቸው፥ እኔ ባርያህ ነኝና ነፍሴን የሚያስጨንቁአትን ሁሉ አጥፋቸው።


ወደ እኔ ተመልከት፥ ራራልኝ፥ ኃይልህን ለአገልጋይህ፥ ማዳንህንም ለአግልጋይቱ ልጅ ለእኔ ስጥ።


የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ጌታ ቀብቶኛልና፥ ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል።


የሚያገለግለኝ ቢኖር ይከተለኝ፤ እኔም ባለሁበት አገልጋዬ ደግሞ በዚያ ይሆናል፤ የሚያገለግለኝም ቢኖር አብ ያከብረዋል።


የእርሱ የምሆንና ደግሞ የማመልከው የእግዚአብሔር መልአክ በዚች ሌሊት በአጠገቤ ቆሞ ነበርና፤ እርሱም


አሁን ግን ከኃጢአት ነፃ ወጥታችሁ ለእግዚአብሔርም ባርያዎች ሆናችኋል፥ ፍሬያችሁም ቅድስና ነው፤ መጨረሻውም የዘለዓለም ሕይወት ነው።


የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ያዕቆብ ለተበተኑ ለዐሥራ ሁለቱ ነገዶች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን።