La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 112:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ክፉ ዜናን አይፈራም፥ ልቡ የጸና፥ በጌታም የታመነ ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ክፉ ወሬ አያሸብረውም፤ ልቡ እግዚአብሔርን በመተማመን የጸና ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እምነቱ ጽኑ ስለ ሆነና በእግዚአብሔርም ስለሚተማመን፥ ክፉ ወሬ አያስደነግጠውም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ድሃ​ውን ከም​ድር የሚ​ያ​ነሣ፥ ምስ​ኪ​ኑ​ንም ከመ​ሬት ከፍ ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ፤

Ver Capítulo



መዝሙር 112:7
20 Referencias Cruzadas  

በዚያን ጊዜ በእውነት ፊትህን ያለ ነውር ታነሣለህ፥ ትበረታለህ፥ አትፈራምም።


ጌታ ከጎኔ ነው፥ አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል?


ጌታን ከእኔ ጋር አክብሩት፥ በአንድነትም ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ።


በደል ተረከዜን በከበበኝ ጊዜ በክፉ ቀን ለምን እፈራለሁ?


ለእግሮቼ ወጥመድን አዘጋጁ፥ ነፍሴንም አጐበጡአት፥ ጉድጓድ በፊቴ ቈፈሩ፥ በእርሱም ወደቁ።


መድኃኒቴና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፥ ጠንካራ ዓለቴና መጠለያዬ እግዚአብሔር ነው።


ሰዎች ሁሉ ፈሩ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ ተናገሩ፥ ሥራውንም አስተዋሉ።


የሚሰማኝ ግን ተረጋግቶ ይቀመጣል፥ ከክፉም ሥጋት ያርፋል።”


በመታገሣችሁም ነፍሳችሁን ታተርፋላችሁ።


ጦርንና ሁከትንም በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ አስቀድሞ ይሆን ዘንድ ግድ ነውና፤ ነገር ግን መጨረሻው ወዲያው አይሆንም።”


“ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ።


ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ።


ጳውሎስ ግን መልሶ “እያለቀሳችሁ ልቤንም እየሰበራችሁ ምን ማድረጋችሁ ነው? እኔ ስለ ጌታ ስለ ኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመሞት እንኳ ተሰናድቼአለሁ እንጂ ለእስራት ብቻ አይደለም፤” አለ።


ስለዚህ እናንተ ሰዎች ሆይ! አይዞአችሁ፤ እንደ ተናገረኝ እንዲሁ እንዲሆን እግዚአብሔርን አምናለሁ።