La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 108:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ፥ በቀኝህ አድን አድምጠኝም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ከመቅደሱ ተናገረ፤ “ደስ እያለኝ ሴኬምን እከፋፍላለሁ፤ የሱኮትንም ሸለቆ እለካለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር በመቅደሱ ሆኖ እንዲህ አለ፦ “ድል አድርጌ ሴኬምን እሸነሽናለሁ፤ የሱኮትንም ሸለቆ ለሕዝቤ አከፋፍላለሁ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሚ​ከ​ራ​ከ​ርም ጊዜ ተረ​ትቶ ይውጣ፤ ጸሎ​ቱም በደል ትሁ​ን​በት።

Ver Capítulo



መዝሙር 108:7
13 Referencias Cruzadas  

ያዕቆብ ግን ወደ “ሱኮት” ሄደ፥ ከዚያም ለራሱ ቤትን ሠራ፥ ለከብቶቹም ዳሶችን አደረገ። ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም “ሱኮት” ብሎ ጠራው።


ወዳጆችህ እንዲድኑ በቀኝህ አድን፥ አድምጠኝም።


ጌታ እግዚአብሔር፦ እናንተን በሜንጦ፥ ትሩፋቶቻችሁንም በመንጠቆ የሚወስዱበት ቀን፥ እነሆ፥ በላያችሁ ይመጣል ብሎ በቅዱስነቱ ምሎአል።


የምናሴም ግዛት ከአሴር ጀምሮ በሴኬም ፊት ለፊት እስካለው እስከ ሚክምታት ድረስ ነበረ፤ ድንበሩም በቀኝ በኩል ወደ ዓይንታጱዋ ሰዎች አለፈ።


በንፍታሌም ባለው በተራራማው አገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው አገር ሴኬምን፥ በይሁዳም ባለው በተራራማው አገር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያት-አርባቅን ለዩ።


ኢያሱም የእስራኤልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴኬም ሰበሰበ፥ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች አለቆቻቸውንም ፈራጆቻቸውንም ሹማምንቶቻቸውንም ጠራ። እነርሱም በጌታ ፊት ቆሙ።


ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን፥ ከምሕረቱ ብዛት በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እና አባት ይመስገን፤


እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩትም በእርሱ በማመናችሁ መግለጽ በማይቻልና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ብሎአችኋል።