Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 33:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ያዕቆብ ግን ወደ “ሱኮት” ሄደ፥ ከዚያም ለራሱ ቤትን ሠራ፥ ለከብቶቹም ዳሶችን አደረገ። ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም “ሱኮት” ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ያዕቆብ ግን ወደ ሱኮት ሄደ፤ እዚያም ለራሱ መጠለያ፣ ለከብቶቹም በረት ሠራ፤ ከዚህም የተነሣ የቦታው ስም ሱኮት ተባለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ያዕቆብ ግን ወደ ሱኮት አመራ፤ እዚያም ለራሱ ቤትና ለከብቶቹም መጠለያ ሠራ፤ ስለዚህ ያ ስፍራ ሱኮት ተባለ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ያዕ​ቆብ ግን በሰ​ፈሩ አደረ፤ በዚ​ያም ለእ​ርሱ ቤትን ሠራ፤ ለከ​ብ​ቶ​ቹም ዳሶ​ችን አደ​ረገ፤ ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያን ቦታ ስም ማኅ​ደር ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ያዕቆብ ግን ወደ ሱኮት ሄደ በዚያም ለእርሱ ቤትን ሠራ ለከብቶች ዳሶችን አደረገ፤ ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም ሱኮት ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 33:17
10 Referencias Cruzadas  

ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ፥ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው።


የሱኮትንም ሰዎች፥ “የምድያምን ነገሥታት ዜባሕንና ጻልሙናን በማሳደድ ላይ ስለ ሆንኩ የተከተሉኝም ሰዎች ስለ ደከሙ ብኝ እባካችሁ የሚበሉትን እንጀራ ስጧቸው” አላቸው።


በሸለቆውም ቤትሀራም፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የተቀረውም የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ነበረ። ድንበሩም ዮርዳኖስና በምሥራቅ በኩል ባለው በዮርዳኖስ ማዶ የኪኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ነበር።


ጌዴዎን የከተማይቱን አለቆች ወሰደ፤ በምድረ በዳ እሾኽና አሜኬላ በመቅጣት የሱኮትን ሰዎች ትምህርት ሰጣቸው።


ከዚያም ወደ ጵኒኤል ሰዎች ሄዶ ያንኑ ጥያቄ አቀረበላቸው፤ የእነርሱም መልስ የሱኮት ሰዎች ከሰጡት መልስ ጋር ተመሳሳይ ነበር።


ንጉሥ ሰሎሞን እነዚህን ሁሉ ያሠራው በዮርዳኖስ ሸለቆ በሱኮትና ጻርታን መካከል በሚገኘው በብረት ማቅለጫ ስፍራ ነበር።


እርሱም የሱኮት ሰው የሆነ አንድ ወጣት ማረከ፤ መረመረውም፤ ወጣቱም የሰባ ሰባት የሱኮት ሹማምንትና የከተማይቱንም አለቆች ስም ጻፈለት።


ከሱኮትም ወጡ፥ በምድረ በዳውም ዳር በኤታም ሰፈሩ።


የእስራኤልም ልጆች ከራዓምሴስ ወደ ሱኮት በእግር ተጓዙ፤ ከሕፃናቱም ሌላ ስድስት መቶ ሺህ ሰው የሚያህሉ ነበሩ።


ዔሳውም በዚያኑ ቀን ወደ ሴይር መንገዱ ተመለሰ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios