ንጉሡም በስፍራው ቆሞ ጌታን ተከትሎ እንዲሄድ፥ ትእዛዛቱንና ምስክሩን ሥርዓቱንም በፍጹም ልቡና በፍጹም ነፍሱ እንዲጠብቅ፥ በዚህም መጽሐፍ የተጻፈውን የቃል ኪዳን ቃል እንዲያደርግ በጌታ ፊት ቃል ኪዳን አደረገ።
መዝሙር 103:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃል ኪዳኑን በሚጠብቁ፥ ትእዛዙንም ያደርጉአት ዘንድ በሚያስቡ ላይ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኪዳኑን በሚጠብቁት ላይ፣ ትእዛዙንም ለመፈጸም በሚተጕት ላይ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም የሚያደርገው ቃል ኪዳኑን ቢጠብቁ፥ ትእዛዙንም በታማኝነት ቢፈጽሙ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ረጃጅም ተራራዎች ለዋሊያዎች፥ ድንጋዮችም ለአሽኮኮዎች መሸሻ ናቸው። |
ንጉሡም በስፍራው ቆሞ ጌታን ተከትሎ እንዲሄድ፥ ትእዛዛቱንና ምስክሩን ሥርዓቱንም በፍጹም ልቡና በፍጹም ነፍሱ እንዲጠብቅ፥ በዚህም መጽሐፍ የተጻፈውን የቃል ኪዳን ቃል እንዲያደርግ በጌታ ፊት ቃል ኪዳን አደረገ።
ሰዎች ከጥንት ጀምሮ ማንም አልሰሙም፥ የትኛውም ጆሮ አልተቀበለውም፥ ለሚጠብቁህ ከምትሠራላችው ከአንተ አምላካችን በቀር ሌላ ማንም አላየውም።
ጌታ አምላካችሁ ከእናንተ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ፥ ጌታ አምላካችሁም የከለከለውን በማናቸውም መልክ የተቀረጸውን ምስል እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ።
“እንዲህም ይሆናል፥ ይህችን ፍርድ ሰምተህ ብትጠብቃት ብታደርጋትም፥ ጌታ አምላካችሁ ለአባቶችህ የማለውን ቃል ኪዳንና ዘላለማዊ ፍቅር ለአንተም ይጠብቅልሃል፥
አንተም ጌታ አምላካችሁ እርሱ እግዚአብሔር እንደሆነ፥ ለሚወዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደሆነ እወቅ፤
እንግዲህ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! እግዚአብሔርን ለማስደሰት እንዴት መመላለስ እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ ተቀብላችኋል፤ በእርግጥም እየተመላለሳችሁ ነው፤ ከዚህም በበለጠ አብዝታችሁ እንድታደርጉት በጌታ በኢየሱስ እንለምናችኋለን፤ እንመክራችኋለንም።