ምሳሌ 6:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከንቱና ክፉ ሰው ጠማማ ንግግር ይዞ ይዞራል፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምናምንቴና ጨካኝ ሰው፣ ነውረኛ አንደበቱን ይዞ የሚዞር፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባለጌና ክፉ ሰው በየቦታው እየዞረ ነገር እያጣመመ ያወራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዓመፀኛና ሰነፍ የሆነ ሰው ቀና ያልሆኑ መንገዶችን ይሄዳል፤ |
በአንደኛው ቅርጫት አስቀድሞ እንደ ደረሰ በለስ የሚመስል እጅግ መልካም በለስ ነበረበት፤ በሁለተኛውም ቅርጫት ከክፋቱ የተነሣ ሊበላ የማይችል እጅግ ክፉ በለስ ነበረበት።
ከዚህም ጎን ለጎን ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራ መፍታትን ይማራሉ፤ ሥራ ፈቶችም ብቻ ሳይሆኑ የማይገባቸውን እየተናገሩ ሰውን የሚያሙና በነገር ጣልቃ የሚገቡ ይሆናሉ።
ምላስም እንደ እሳት ናት፤ በሰውነት ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ የክፋት ዓለም ናት፤ ሰውነትን ሁሉ ታረክሳለች፤ ደግሞም የፍጥረትን ሩጫ ታቃጥላለች፤ ራሷም በገሃነም ትቃጠላለች።
ታላቅ ወንድሙ ኤሊአብ፥ ዳዊት ከሰዎች ጋር ሲነጋገር በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጥቶ፥ “ለምን ወደዚህ ወረድህ? እነዚያንስ ጥቂት በጎች በምድረ በዳ ለማን ተውካቸው? ዕብሪትህንና የልብህን ክፋት ዐውቃለሁ፤ የመጣኸው ጦርነቱን ለማየት ብቻ ነው” አለው።