ክፉ ሰዎች ሥልጣን ሲይዙ ሕግ መጣስ ይበዛል፥ ጻድቃን ግን ውደቀታቸውን ያያሉ።
ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ኀጢአት ይበዛል፤ ጻድቃን ግን የእነርሱን ውድቀት ያያሉ።
ክፉ ሰዎች ሥልጣን ሲይዙ ሕግ መተላለፍ ይበዛል፤ ደጋግ ሰዎች ግን የክፉ ሰዎችን ውድቀት ሳያዩ አይሞቱም።
በጠላቶቹ ላይ እስኪኮራ ድረስ ልቡ ጽኑ ነው፥ አይፈራምም።
በጌታ ተስፋ አድርግ፥ መንገዱንም ጠብቅ፥ ምድርንም ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፥ ክፉዎችም ሲጠፉ ታያለህ።
ብመለስ ግን አጣሁት፥ ፈለግሁት ቦታውንም አላገኘሁም።
ድስታችሁ የእሾኽን መቀጣጠል ከመስማቱ በፊት፥ ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ጠራርጎ ያጠፋል።
በዐይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ቅጣት ታያለህ።
እንደ ጐሽ አጠነከርከኝ፥ በአዲስ ዘይትም ቀባኸኝ።
አቤቱ፥ አንተ ግን ለዘለዓለም ልዑል ነህ፥
ጻድቅ ስለ ኀጥእ ቤት ያስባል፥ ኀጥኣንም ለጥፋት እንደ ተገለበጡ።
ጻድቃን በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል፥ ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ግን ሕዝብ ያለቅሳል።
“ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን፥ ሐዋርያትና ነቢያት ሆይ! ስለተፈረደባት በእርሷ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።”