17 ልጅህን ቅጣ ዕረፍትንም ይሰጥሃል፥ ለነፍስህም ደስታን ይሰጣታል።
17 ልጅህን ቅጣው፤ ሰላም ይሰጥሃል፤ ነፍስህንም ደስ ያሰኛታል።
17 ልጅህን ቅጣ፤ ዕረፍትና ሰላም በማግኘት ደስ ትሰኛለህ።
የሰሎሞን ምሳሌዎች። ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፥ አላዋቂ ልጅ ግን ለእናቱ ኀዘን ነው።
በበትር ከመምታት የሚራራ ሰው ልጁን ይጠላል፥ ልጁን የሚወድድ ግን ተግቶ ይገሥጸዋል።
ተስፋ ገና ሳለች ልጅህን ገሥጽ፥ መሞቱንም አትሻ።
ቂልነት በልጅ ልብ ውስጥ ተተብትቧል፥ የተግሣጽ በትር ግን ነፃ ያደርገዋል።
በትርና ተግሣጽ ጥበብን ይሰጣሉ፥ ያልተቀጣ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል።