ማር፥ እርጎ፥ በጎችና የላም አይብ እንዲበሉ ለዳዊትና ለሕዝቡ አመጡላቸው፤ ይህን ያደረጉትም፥ “ሕዝቡ በምድረ በዳ ተርቧል፤ ደክሞአል፤ ተጠምቶአል” ብለው ነው።
ምሳሌ 21:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኀጥእ ቀኑን ሁሉ ምኞትን ይመኛል፥ ጻድቅ ግን ይሰጣል፥ አይሰስትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ ሰው ቀኑን ሙሉ ይመኛል፤ ጻድቅ ግን አንዳች ሳያስቀር ይሰጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰነፍ ሰው ዘወትር የሚመኘው ብዙ ነገር ለማግኘት ነው፤ ደግ ሰው ግን በልግሥና ይሰጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኃጥእ ቀኑን ሁሉ ክፉ ምኞትን ይመኛል፥ ጻድቅ ግን ዐውቆ ይራራል፥ ይመጸውታልም። |
ማር፥ እርጎ፥ በጎችና የላም አይብ እንዲበሉ ለዳዊትና ለሕዝቡ አመጡላቸው፤ ይህን ያደረጉትም፥ “ሕዝቡ በምድረ በዳ ተርቧል፤ ደክሞአል፤ ተጠምቶአል” ብለው ነው።