ጠቢብ የኃያላንን ከተማ ይገባባታል፥ የሚታመኑበትንም ኃይል ያፈርሳል።
ጠቢብ የኀያላንን ከተማ ቅጥር ጥሶ ይገባል፤ መታመኛ ምሽጋቸውንም ያፈርሳል።
ብልኅ የጦር መሪ በብርቱ ሠራዊት የተጠበቀውን ከተማ ድል አድርጎ ይይዛል፤ የተማመኑባቸውንም ምሽጎች ያፈራርሳል።
ጠቢብ የጸናች ከተማን ይገባባታል፥ ክፉዎች የሚተማመኑበትንም ኀይል ያፈርሳል።
ጠቢብ ሰው ብርቱ ነው፥ አዋቂም ሰው ኃይሉን ያበዛል።
በከተማ ከሚኖሩ ከዐሥር ገዢዎች ይልቅ ጥበብ ጠቢብን ታበረታለች።