ምሳሌ 2:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ በመሥራት ደስ የሚላቸው በጠማማነትም ሐሤትን የሚያደርጉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ በመሥራት ደስ የሚላቸው፣ በክፋት ጐዳና ሐሤት የሚያደርጉ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱን ደስ የሚያሰኛቸው ቀናውን ነገር ማጣመምና ተንኰል የተሞላበት ክፉ ሥራ መሥራት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉ በመሥራት ደስ ለሚላቸው ክፋትንም በመመለስ ሐሤትን ለሚያደርጉ፥ |
በዚያ ቀን በእኔ ላይ አምፀሽ በሠራሽው ሥራ ሁሉ አታፍሪም፤ በኩራትሽ የተደሰቱትን ከመካከልሽ አወጣለሁና፥ አንቺም በቅዱስ ተራራዬ ላይ ዳግመኛ አትታበዪም።
“እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉ ሞት ይገባቸዋል” የሚለውን ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን ሕግ ቢያውቁም፥ እነዚህን ነገሮች ማድረግ ብቻ ሳይሆን፥ እንዲህ የሚያደርጉትንም ያበረታታሉ።