የጠብ መጀመሪያ እንደ ውኃ አፈሳሰስ ነው፥ ስለዚህ ጠብ ሳይበረታ አንተ ክርክርን ተው።
ጠብ መጫር ግድብን እንደ መሸንቈር ነው፤ ስለዚህ ጠብ ከመጫሩ በፊት ከነገር ራቅ።
የጥል መነሻ መፍረስ እንደ ጀመረ ግድብ ነው፤ ስለዚህ ጥል ከማስከተሉ በፊት ክርክርን አቁም።
የጠብ መጀመሪያ ውኃን መድፈን ነው። የጽድቅ መጀመሪያ በነገር መሠልጠንን ይሰጣል፥ የችጋር አበጋዝ ጠብና ክርክር ነው።
ንጉሡ ወደ ጌልገላ ሲሄድ፥ ኪምሃም አብሮት ሄደ። የይሁዳ ሠራዊት በሙሉ እንዲሁም ግማሹ የእስራኤል ሠራዊት ንጉሡን አጅበው አሻገሩት።
አብያና ሕዝቡ በታላቅ ውግያ ድል አደረጓቸው፤ ከእስራኤልም አምስት መቶ ሺህ የተመረጡ ሰዎች ተገድለው ወደቁ።
የአባቶቻቸውንም አምላክ ጌታን ትተው ነበርና የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በአንድ ቀን ከይሁዳ መቶ ሃያ ሺህ ገደለ፤ ሁሉም ጽኑዓን ነበሩ።
በትዕቢት ጠብ ብቻ ይሆናል፥ ጥበብ ግን ምክርን በሚቀበሉ ዘንድ ናት።
ለትግሥተኛ ሰው ብዙ ማስተዋል አለው፥ ቁጡ ግን ስንፍናውን ከፍ ከፍ ያደርጋል።
የለዘበች መልስ ቁጣን ትመልሳለች፥ ሸካራ ቃል ግን ቁጣን ታስነሣለች።
ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ ስሜቱን የሚገዛ ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል።
ዓመፃን የሚወድድ ክርክርን ይወድዳል፥ ደጁንም ዘለግ የሚያደርግ ውድቀትን ይሻል።
ሰውን ጠቢብ አእምሮው ከቁጣ ያዘገየዋል፥ ለበደለኛውም ይቅር ይል ዘንድ ክብር ይሆንለታል።
ከክርክር ይርቅ ዘንድ ለሰው ክብሩ ነው፥ ሰነፍ ሁሉ ግን እንዲህ ባለ ነገር ይጣመራል።
ባልንጀራህ ባሳፈረህ ጊዜ ኋላ እንዳትጸጸት ለሙግት ወደ ሽንጎ ፈጥነህ አትውጣ፥
ከሰል ፍምን እንጨትም እሳትን እንዲያበዛ፥ እንዲሁ ቁጡ ሰው ጠብን ያበዛል።
ቁጡ ሰው ክርክርን ያነሣሣል። ወፈፍተኛ ሰውም ኃጢአትን ያበዛል።
ቢቻላችሁ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።
በጸጥታ ለመኖር እንድትተጉ፥ በራሳችሁም ጉዳይ ላይ እንድታተኩሩ፥ እንዳዘዝናችሁም በራሳችሁ እጅ እንድትሰሩ እንለምናችኋለን፤