የሕዝቡ መሪዎች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ ከቀረው ሕዝብ ከአሥሩ አንዱ እጅ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፥ የቀሩት ዘጠኙ ደግሞ በሌሎች ከተሞች እንዲቀመጡ ዕጣ ተጣጣሉ።
ምሳሌ 16:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዕጣ በጉያ ይጣላል፥ መደብዋ ሁሉ ግን ከጌታ ዘንድ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕጣ በጕያ ውስጥ ይጣላል፤ ውሳኔው በሙሉ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ዕጣ ይጥላሉ፤ ነገር ግን ውሳኔውን የሚሰጠው እግዚአብሔር ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የበደለኛ ሰው በደሉ ሁሉ ወደ ጕያው ይመለሳል። ጽድቅ ሁሉ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። |
የሕዝቡ መሪዎች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ ከቀረው ሕዝብ ከአሥሩ አንዱ እጅ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፥ የቀሩት ዘጠኙ ደግሞ በሌሎች ከተሞች እንዲቀመጡ ዕጣ ተጣጣሉ።
የባቢሎን ንጉሥ ምዋርቱን ያምዋርት ዘንድ በመንታ መንገድ ላይ በሁለቱ መንገዶች ራስ ላይ ቆሞ ነበር፤ ፍላጾችን ወዘወዘ፥ ከተራፊምም ጠየቀ፥ ጉበትም ተመለከተ።
እርስ በእርሳቸውም፦ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንደመጣብን እንድናውቅ ኑ፥ ዕጣ እንጣጣል” ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፥ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ።
በሰባትም ክፍል ይከፍሉታል፤ ይሁዳ በደቡብ በኩል ባለው ግዛት ውስጥ ይቀመጣል፤ የዮሴፍ ወገኖች በሰሜን በኩል ባለው ግዛት ውስጥ ይቀመጣሉ።
ነገ ጧት በየነገዳችሁ ትቀርባላችሁ፤ ጌታም የሚለየው ነገድ በየወገኖቹ ይቀርባል፤ ጌታም የሚለየው ወገን በየቤተ ሰቦቹ ይቀርባል፤ ጌታም የሚለየው ቤተሰብ በየሰዉ ይቀርባል።
ዛሬ ግን ከመከራችሁና ከጭንቃችሁ ሁሉ የሚያድናችሁን አምላካችሁን ንቃችሁ፤ ‘የለም፤ ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁ። ስለዚህ በየነገዳችሁና በየወገናችሁ ሆናችሁ በጌታ ፊት ቅረቡ።”