| ሕዝቅኤል 21:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 የባቢሎን ንጉሥ ምዋርቱን ያምዋርት ዘንድ በመንታ መንገድ ላይ በሁለቱ መንገዶች ራስ ላይ ቆሞ ነበር፤ ፍላጾችን ወዘወዘ፥ ከተራፊምም ጠየቀ፥ ጉበትም ተመለከተ።Ver Capítulo አዲሱ መደበኛ ትርጒም21 የባቢሎን ንጉሥ በጥንቈላ ምሪት ለማግኘት በመንታ መንገድ ላይ በሁለቱ ጐዳናዎች መጋጠሚያ ላይ ይቆማል፤ ቀስቶቹን በመወዝወዝ ዕጣ ይጥላል፤ አማልክቱን ያማክራል፤ ጕበትንም ይመረምራል።Ver Capítulo አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 የባቢሎን ንጉሥ በመስቀለኛ መንገዶቹ መታጠፊያ አጠገብ ይቆማል፤ በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለበት ለማወቅ ፍላጻዎችን ይወረውራል፤ ጣዖቶቹንም ምክር ይጠይቃል፤ ለመሥዋዕት ከታረደ እንስሳ የጒበት ሞራ ወስዶም ይመረምራል።Ver Capítulo የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 የባቢሎን ንጉሥ ምዋርቱን ያምዋርት ዘንድ፥ በትሩን ያነሣ ዘንድ፥ ጣዖቱንም ይጠይቅ ዘንድ በሁለት መንገዶች ራስ ላይ ይቆማል።Ver Capítulo መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 የባቢሎን ንጉሥ ምዋርቱን ያምዋርት ዘንድ በመንታ መንገድ ላይ በሁለቱ መንገዶች ራስ ላይ ቆሞ ነበር፥ ፍላጾችን ወዘወዘ፥ ከተራፊምም ጠየቀ፥ ጉበትም ተመለከተ።Ver Capítulo |