ምሳሌ 14:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለትግሥተኛ ሰው ብዙ ማስተዋል አለው፥ ቁጡ ግን ስንፍናውን ከፍ ከፍ ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታጋሽ ሰው ትልቅ ማስተዋል አለው፤ ግልፍተኛ ሰው ግን ቂልነትን ያሳያል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትዕግሥተኛ ብትሆን አስተዋይ መሆንህን ትገልጣለህ፤ ቊጡ ብትሆን ግን ስንፍናህን ታሳያለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትዕግሥተኛ ሰው ጥበብ የበዛለት ይሆናል፤ ትዕግሥት የጐደለው ሰው ግን ሰነፍ ነው፤ |
ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ እንዳታለሉት በተረዳ ጊዜ እጅግ ተቆጣ፥ ወታደሮችን ልኮ ከሰብአ ሰገል በተረዳው ዘመን መሠረት፥ ሁለት ዓመትና ከዚያም በታች የሆኑትን በቤተ ልሔምና በአካባቢዋ የነበሩትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።