ምሳሌ 1:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፥ እኔ ግን አልመልስም፥ ተግተው ይሹኛል፥ ነገር ግን አያገኙኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚያ ጊዜ ይጠሩኛል፤ እኔ ግን አልመልስላቸውም፤ አጥብቀው ይፈልጉኛል፤ ነገር ግን አያገኙኝም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ እኔን ጥበብን ትጣራላችሁ፤ እኔ ግን አልመልስላችሁም፤ በየቦታውም ትፈልጉኛላችሁ፤ ነገር ግን አታገኙኝም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ግን በጠራችሁኝ ጊዜ እኔ አልሰማችሁም፤ ክፉዎች ይሹኛል፥ ነገር ግን አያገኙኝም። |
ለውዴ ከፈትሁለት፥ ውዴ ግን ፈቀቅ ብሎ አልፎ ነበር። ነፍሴ ከመራቁ የተነሣ ደነገጠች፥ ፈለግሁት፥ አላገኘሁትም፥ ጠራሁት፥ ነገር ግን አልመለሰልኝም።
እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፤ ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤ አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤
በጾሙ ጊዜ ልመናቸውን አልሰማም፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቁርባን ባቀረቡ ጊዜ አልቀበላቸውም፤ ይልቁንም በሰይፍና በራብ በቸነፈርም አጠፋቸዋለሁ” አለኝ።