ፊልጵስዩስ 3:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ በክርስቶስ ኢየሱስም የምንመካ በሥጋም የማንታመን በእውነትም ከተገረዙት ወገን የሆንን ነንና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛ በእውነት የተገረዝን በእግዚአብሔር መንፈስ የምናመልክ፣ በክርስቶስ ኢየሱስ የምንመካ፣ በሥጋም የማንታመን ነንና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ እግዚአብሔርን በመንፈስ የምናመልክና በውጭ በሚታየው ሥርዓት ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ የምንመካ ስለ ሆንን በእውነት ተገርዘናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ግዙራንስ እግዚአብሔርን በመንፈስ የምናገለግለውና የምናመልከው እኛ ነን፤ እኛም በኢየሱስ ክርስቶስ እንመካለን እንጂ በሥጋችን የምንመካ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ በክርስቶስ ኢየሱስም የምንመካ በሥጋም የማንታመን እኛ የተገረዝን ነንና። |
እናንተም የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሆይ! ስለ ሥራችሁ ክፋት ቁጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳያቃጥል፥ ለጌታ እራሳችሁን ግረዙ፥ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ።”
እንዲሁም የእስራኤል ቤት ሁሉ ልባቸው ያልተገረዘ ነውና፥ አሕዛብም ሁሉ ያልተገረዙ ናቸውና ግብጽንና ይሁዳን፥ ኤዶምያስንም፥ የአሞንንም ልጆች፥ ሞአብንም፥ በምድረ በዳም የተቀመጡትን ጠጉራቸውን በዙሪያ የተላጩትን ሁሉ በዚያን ዘመን እቀጣለሁ።”
“ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በሕዝቦች መካከል ታላቅ ይሆናል፤ በሁሉም ስፍራ ለስሜ ዕጣን ያመጣሉ፥ ንጹሕ ቁርባንም ያቀርባሉ፤ ስሜ በሕዝቦች መካከል ታላቅ ይሆናል፥” ይላል የሠራዊት ጌታ።
አሁን ግን ለእርሱ ታስረን ከነበርንበት በመሞት ከሕግ ተፈትተናል፤ ስለዚህም በአሮጌው በፊደል ሳይሆን በአዲስ በመንፈስ ኑሮ እናገለግላለን።
እንደገና የፍርሃት ባርያ የሚያደርጋችሁን መንፈስ አልተቀበላችሁምና፥ ነገር ግን “አባ! አባት!” ብለን የምንጠራበትን የልጅነት መንፈስ ተቀብላችኋል።
ጌታ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ እንድትወደው፥ በሕይወትም እንድትኖር፥ አምላክህ ጌታ የአንተንና የዘርህን ልብ ይገርዛል።
የኢየሱስ ክርስቶስ ባርያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ፥ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤
እኔ ግን አሁን ይህን አላገኘሁትም ወይም አሁን ፍጹም ለመሆን አልበቃሁም፤ ዳሩ ግን ክርስቶስ ኢየሱስ የራሱ አድርጎኛልና ይህን የራሴ ለማድረግ ወደ ፊት እሮጣለሁ።