Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ፊልጵስዩስ 3:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ከፍ ከፍ ያለውን የመጠራት ሽልማት እንዳገኝ ወደ ግቡ እሮጣለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ላይ ስለ ጠራኝ፣ ሽልማት ለመቀዳጀት ወደ ግቡ እፈጥናለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሽልማቴንም ለማግኘት በፊቴ ወዳለው ግብ እሮጣለሁ፤ ይህም ሽልማት እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ወደ ላይ ጠርቶ የሚሰጠኝ ሕይወት ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የኋ​ላ​ዬን እረ​ሳ​ለ​ሁና፥ ወደ ፊቴም ፈጥኜ እገ​ሠ​ግ​ሣ​ለ​ሁና፤ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ከፍ ከፍ ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የጥሪ ዋጋ ለማ​ግ​ኘት ወደ ግቡ እፈ​ጥ​ና​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ፊልጵስዩስ 3:14
20 Referencias Cruzadas  

“ሕግና ነቢያት እስከ ዮሐንስ ነበሩ፤ ከዚያ ጀምሮ የእግዚአብሔር መንግሥት ይሰበካል፤ ሁሉም ወደ እርሷ ለመግባት ይታገላል።


እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትምና።


በሩጫ መወዳደሪያ ስፍራ የሚሮጡት ሁሉ እንደሚሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ሽልማቱን ዋጋውን እንደሚቀበል አታውቁምን? ስለዚህ እናንተም እንድትቀበሉ ሩጡ።


ቀላል የሆነው ጊዜያዊ መከራችን ከመመዘኛዎች ሁሉ ለሚያልፈው ለዘላለማዊ ክብር ያዘጋጀናል።


እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ በክርስቶስ ኢየሱስም የምንመካ በሥጋም የማንታመን በእውነትም ከተገረዙት ወገን የሆንን ነንና።


ራስን ማዋረድና የመላእክትን አምልኮ እየወደደ፥ ባየውም ራእይ ላይ በጽኑ እየተመረኮዘ፥ በሥጋዊም አእምሮ በከንቱ እየታበየ ማንም አይፍረድባችሁ፤


በመሆኑም ወደ መንግሥቱ ወደ ክብሩም ለጠራችሁ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ እንድትመላለሱ እየመከርናችሁ፥ እያጸናናችሁና እየመሰከርንላችሁ ነበር።


እንደ ሥራችን መጠን ሳይሆን እንደ ራሱ ዕቅድና እንደ ጸጋው መጠን አዳነን፥ በቅዱስም አጠራር ጠራን፤ ይህም ጸጋ ከዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፤


ስለዚህ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ! የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤


ስለዚህ የክርስቶስን የመጀመሪያ ትምህርት አልፈን ወደ ፍጻሜ እንሂድ፤ መሠረትን ደግመን አንመሥርት፤ እርሱም ከሞተ ሥራ ንስሓና በእግዚአብሔር እምነት፥


ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።


በክርስቶስ ወደ ዘለዓለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ፥ እርሱ ራሱ ያበረታችኋል፤ ያጸናችኋል፤ ያቆማችኋል፤ ይመሠርታችኋልም።


በመለኮቱ ኃይል በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ሰጠን።


እኔም ድል እንደ ነሣሁ፥ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፥ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ እንዲቀመጥ አደርገዋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos