Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሮሜ 8:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እንደገና የፍርሃት ባርያ የሚያደርጋችሁን መንፈስ አልተቀበላችሁምና፥ ነገር ግን “አባ! አባት!” ብለን የምንጠራበትን የልጅነት መንፈስ ተቀብላችኋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እንደ ገና የፍርሀት ባሪያ የሚያደርጋችሁን መንፈስ ሳይሆን፣ “አባ፣ አባት” ብለን የምንጠራበትን የልጅነት መንፈስ ተቀብላችኋልና፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ስለዚህ “አባ! አባታችን ሆይ!” ብላችሁ የምትጠሩበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ በፍርሃት ለመኖር እንደገና የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ዳግ​መ​ናም አባ አባት ብለን የም​ን​ጮ​ህ​በ​ትን የል​ጅ​ነት መን​ፈስ ተቀ​በ​ላ​ችሁ እንጂ እንደ ገና ለፍ​ር​ሀት የባ​ር​ነት መን​ፈ​ስን አል​ተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁ​ምና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 8:15
30 Referencias Cruzadas  

ሙሴንም እንዲህ አሉት፦ “አንተ ተናገረን እኛም እንሰማለን፤ ነገር ግን እንዳንሞት እግዚአብሔር አይናገረን።”


በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ሁሉ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘለዓለም ስም እሰጣቸዋለሁ።


እኔ ግን፦ “‘ከወንዶች ልጆች ጋር እንዴት አስቀምጥሻለሁ? ያማረችውንስ ምድር እጅግ የከበረችውን የአሕዛብን ርስት እንዴት እሰጥሻለሁ? ብዬ ነበር። ደግሞ፦ አባቴ ብለሽ ትጠሪኛለሽ፤ እኔንም ከመከተል አትመለሽም ብዬ ነበር።


የእስራኤልም ልጆች ሙሴን እንዲህ አሉት፦ “እነሆ፥ እንሞታለን፥ እንጠፋለን፥ ሁላችንም እንጠፋለን።


ስለፈራሁም ሄጄ መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ የራስህ ይኸውልህ’ አለ።


“አባ፤ አባት ሆይ፤ ሁሉ ነገር ይቻልሃልና ይህን ጽዋ ከእኔ አርቀው፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን” አለ።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “በማናቸውም ጊዜ ስትጸልዩ እንዲህ በሉ፦ ‘በሰማያት የምትኖር አባት ሆይ! ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤


“አባት ሆይ! ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ አርቅ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን፤ የአንተ ፈቃድ ይሁን እንጂ፤” እያለ ይጸልይ ነበር።


ኢየሱስንም ባየ ጊዜ ጮኾ በፊቱ ተደፋ፤ በታላቅ ድምፅም፦ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ! አንተ ከእኔ ጋር ምን አለህ? እንዳታሰቃየኝ እለምንሃለሁ፤” አለ።


በጌርጌሴኖንም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች የሚኖረው ሕዝብ ሁሉ በታላቅ ፍርሃት ተይዘው ስለ ነበር ከእነርሱ እንዲሄድ ለመኑት፤ እርሱም በታንኳ ገብቶ ተመለሰ።


እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል፤


ኢየሱስም “ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ ‘እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዐርጋለሁ፤’ ብለሽ ንገሪአቸው፤” አላት።


መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፤ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ፤


ይህንም በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተሰበረ፤ ጴጥሮስንና ሌሎችንም ሐዋርያት “ወንድሞች ሆይ! ምን እናድርግ?” አሉአቸው።


የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን መንፈሱ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክርልናል።


ፍጥረት ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የመንፈስ በኵራት ያለን እኛ ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት በናፍቆት እየተጠባበቅን እኛ ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን።


እንዲሁም ደግሞ መንፈስ በድካማችን ይረዳናል፤ እንዴት መጸለይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በቃላት ሊገለጥ በማይችል መቃተት ለእኛ ያማልድልናል፤


እነርሱም እስራኤላውያን ናቸው፤ ልጅነት፥ ክብር፥ ኪዳን፥ ሕግን መቀበል፥ የቤተ መቅደስ አገልግሎት፥ የተስፋ ቃላትም የእነርሱ ናቸውና፤


እኛ ግን፥ እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር በነፃ የተሰጠንን፥ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም።


ምክንያቱም አንዱ መጥቶ እኛ ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ፥ ወይም ያላገኛችሁትን ልዩ መንፈስ ወይም ያልተቀበላችሁትን ልዩ ወንጌል ሆኖ ብታገኙት፥ በመልካምነታችሁ ትታገሡታላችሁ።


ይህም ወደ ባርነት ሊመልሱን በክርስቶስ ኢየሱስ ያለንን ነጻነታችንን ሊሰልሉ ሾልከው በስውር ስለ ገቡ ስለ ሐሰተኞች ወንድሞች ነበረ።


በነጻነት እንድንኖር ክርስቶስ ነጻ አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በባርነት ቀንበር እንደገና አትያዙ።


በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ልጆቹ እንድንሆን አስቀድሞ ወሰነን።


እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና።


በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ታስረው የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥


አንድ እግዚአብሔር እንዳለ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንትም ቢሆኑ ይህንኑ ያምናሉ፤ በፍርሃትም ይንቀጠቀጣሉ።


በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ነገር ግን ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል፤ ፍርሃት ቅጣት አለው፥ የሚፈራ ሰው በፍቅር ፍጹም አልሆነም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos