ዘኍል 5:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም ሴቲቱን በጌታ ፊት ያቆማታል፥ የሴቲቱንም የተሠራ ጠጉር ይፈታል፥ በእጅዋም የመታሰቢያ የእህል ቁርባን የሆነውን የቅንዓት የእህል ቁርባን ያኖራል፤ ካህኑም እርግማንን የሚያመጣውን መራራ ውኃ በእጁ ይይዛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑ ሴትዮዋን በእግዚአብሔር ፊት እንድትቆም ካደረገ በኋላ የጠጕሯን መሸፈኛ ይገልጣል፤ ስለ ቅናት የቀረበውን የመታሰቢያ ቍርባን በእጇ ያስይዛታል፤ ከዚያም ካህኑ ርግማን የሚያመጣውን መራራ ውሃ በእጁ ይይዛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑም ሴትዮዋን በእግዚአብሔር ፊት ያቁማት፤ የራስዋንም ጠጒር ይፍታ፤ የቅናቱንም የእህል ቊርባን በእጅዋ ላይ ያስቀምጥ፤ በእጁም እርግማንን የሚያመጣ መራራ ውሃ ይያዝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ሴቲቱን በእግዚአብሔር ፊት ያቆማታል፤ የሴቲቱንም ራስ ይገልጣል፤ በእጅዋም ለመታሰቢያ የሚሆነውን የእህል ቍርባን፥ የቅንዐት ቍርባን ያኖራል፤ በካህኑም እጅ ርግማንን የሚያመጣው መራራ ውኃ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ሴቲቱን በእግዚአብሔር ፊት ያቆማታል፥ የሴቲቱንም ራስ ይገልጣል፥ በእጅዋም ለመታሰቢያ የሚሆነውን የእህል ቍርባን፥ ለቅንዓት ቍርባን፥ ያኖራል፤ በካህኑም እጅ እርግማንን የሚያመጣው መራራ ውኃ ይሆናል። |
እኔም ከሞት ይልቅ የመረረ ነገር መርምሬ አገኘሁ፤ እርሷም ልብዋ ወጥመድና መረብ የሆነ፥ እጆችዋም እግር ብረት የሆኑ ሴት ናት፥ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነ ከእርሷ ያመልጣል፥ ኃጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።
ክፋትሽ ይቀጣሻል ክህደትሽ ይገሥጽሻል፤ ጌታን አምላክሽን መተውሽ ምን ያኽል ክፉና መራራ ነገር እንደሆነ እወቂም፥ ተመልከቺም፤ እኔን መፍራት በአንቺ ውስጥ የለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
“የለምጽ ደዌ ያለበት ሰው የሚለብሳቸው ልብሶች የተቀደዱ ይሁኑ፥ የራሱም ጠጉር የተጐሳቈለ ይሁን፥ ከንፈሩንም ይሸፍን፤ ርኩስ ርኩስ ነኝ እያለ ይጩኽ።
ያ ሰው ሚስቱን ወደ ካህኑ ያምጣት፥ የኢፍ መስፈሪያም አሥረኛ እጅ የገብስ ዱቄት የሆነውን ስለ እርሷ የሚቀርበውን ቁርባን ያምጣ፤ የቅንዓት የእህል ቁርባን ነውና፥ በደልንም የሚያስታውስ የመታሰቢያ የእህል ቁርባን ነውና ዘይት አያፍስስበት፥ ዕጣንም አይጨምርበት።
ሴቲቱንም እንዲህ ብሎ ካህኑ ያምላታል፦ ‘ከአንቺ ጋር ሌላ ወንድ ካልተኛ፥ በባልሽም ሥልጣን ሥር እየነበርሽ ራስሽን ለማርከስ ዘወር ካላልሽ፥ እርግማንን ከሚያመጣው ከዚህ መራራ ውኃ የተጠበቅሽ ሁኚ፤
የእነዚህን ሕዝቦች አማልክት ለማምለክ ልቡን ከጌታ ከእግዚአብሔር የሚመልስ ወንድም ሆነ ሴት ቤተሰብም ሆነ ነገድ ዛሬ ከመካከላችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤ ከመካከልህ እንዲህ ያለውን መርዘኛና መራራ የሆነ ፍሬ የሚያበቅል አይገኝባችሁ።
ከዚያም ሳሙኤል፥ “የአማሌቃውያንን ንጉሥ አጋግን አምጡልኝ” አለ። አጋግም፥ “በውኑ ሞት እንዲህ መራራ ነውን?” በማለት እየተንቀጠቀጠ መጣ።