ዘኍል 31:47 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእስራኤል ልጆች ድርሻ ሙሴ ከሰውና ከእንስሳ ከኀምሳ አንድ ወሰደ፥ ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው የጌታን ማደሪያ አገልግሎት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ሰጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእስራኤላውያን እኩሌታ ድርሻ ላይ፣ ሙሴ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ከየዐምሳው ሰውና እንስሳ አንዳንድ መርጦ የእግዚአብሔርን ማደሪያ ድንኳን በኀላፊነት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ሰጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም ድርሻ ሙሴ ከኀምሳው አንድ እስረኛ፥ ከኀምሳው አንድ እንስሳ ወስዶ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት በእግዚአብሔር ድንኳን ላይ ኀላፊነት ላላቸው ለሌዋውያን ሰጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴ ከእስራኤል ልጆች ድርሻ ከሰውና ከእንስሳ ከሃምሳ አንድ ወሰደ፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ድንኳን ሥርዐት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ሰጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእስራኤል ልጆች ድርሻ ሙሴ ከሰውና ከእንስሳ ከአምሳ አንድ ወሰደ፥ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ማደሪያ አገልግሎት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ሰጠ። |
ነገር ግን በእስራኤል ልጆች ጉባኤ ላይ ቁጣ እንዳይወርድ ሌዋውያን በምስክሩ ማደሪያ ዙሪያ ይስፈሩ፤ ሌዋውያንም የምስክሩን ማደሪያ ይጠብቁ።”
ከእስራኤልም ልጆች ድርሻ ከሰዎች ከበሬዎችም ከአህዮችም ከበጎችም ከከብቶችም ሁሉ ከኀምሳ አንድ ትወስዳለህ፥ የጌታንም ማደሪያ አገልግሎት ለሚጠብቁ ለሌዋውያን ትሰጣለህ።”