ዘኍል 31:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)30 ከእስራኤልም ልጆች ድርሻ ከሰዎች ከበሬዎችም ከአህዮችም ከበጎችም ከከብቶችም ሁሉ ከኀምሳ አንድ ትወስዳለህ፥ የጌታንም ማደሪያ አገልግሎት ለሚጠብቁ ለሌዋውያን ትሰጣለህ።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም30 ከእስራኤላውያን እኩሌታ ድርሻ ደግሞ ከሰውም ይሁን ከቀንድ ከብት፣ ከአህያ፣ ከበግ፣ ከፍየል ወይም ከሌሎች እንስሳት ከየዐምሳው አንዳንድ መርጠህ፣ የእግዚአብሔርን ማደሪያ ድንኳን በኀላፊነት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ስጣቸው።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም30 ለቀሩት የማኅበሩ አባላት ከተሰጠውም ክፍል ከኀምሳ እስረኞች አንዱን፥ በዚሁ መጠን ከከብቱ፥ ከአህዮቹ፥ ከበጎቹና ከፍየሎቹ ለይታችሁ ለተቀደሰው ድንኳን ኀላፊዎች ለሆኑት ሌዋውያን ስጡ።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 ከእስራኤልም ልጆች ድርሻ እኩሌታ፥ ከሰዎችም፥ ከበሬዎችም፥ ከበጎችም፥ ከአህዮችም፥ ከእንስሶችም ሁሉ ከአምሳ አንድ ትወስዳለህ፤ የእግዚአብሔርንም ድንኳን ሥርዐት ለሚጠብቁ ለሌዋውያን ትሰጣለህ።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)30 ከእስራኤልም ልጆች ድርሻ ከሰዎች ከበሬዎችም ከአህዮችም ከመንጎችም ከከብቶችም ሁሉ ከአምሳ አንድ ትወስዳለህ፥ የእግዚአብሔርንም ማደሪያ አገልግሎት ለሚጠብቁ ለሌዋውያን ትሰጣለህ። Ver Capítulo |