እነሆ፥ ለእስራኤል ለዘለዓለም እንደ ታዘዘው በጌታ ፊት መዓዛው ያማረውን ሽቶ ዕጣን ለማጠን፥ የተቀደሰውንም ኅብስት ለማኖር፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በጥዋትና በማታ በሰንበታቱም በመባቻዎቹም በአምላካችንም በጌታ በዓላት ለማቅረብ ለአምላኬ ለጌታ ስም ቤት ልሠራለትና ልቀድስለት አሰብሁ።
ዘኍል 28:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕት ሌላ፥ ከመጠጡም ቁርባን ሌላ፥ በየሰንበቱ ሁሉ የምታቀርቡት የሚቃጠለው መሥዋዕት ይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ከመጠጥ ቍርባኑ ጋራ በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ በየሰንበቱ የሚቀርብ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመጠጡ መባና ከሚቀርበው ከዘወትር መሥዋዕት ጋር ይህ የሚቃጠል መሥዋዕት በየሰንበቱ ይቅረብ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕት ሌላ፥ ከመጠጡም ቍርባን ሌላ፥ በየሰንበቱ ሁሉ የምታቀርቡት የሚቃጠለው መሥዋዕት ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕት ሌላ፥ ከመጠጡም ቍርባን ሌላ፥ በየሰንበቱ ሁሉ የምታቀርቡት የሚቃጠለው መሥዋዕት ይህ ነው። |
እነሆ፥ ለእስራኤል ለዘለዓለም እንደ ታዘዘው በጌታ ፊት መዓዛው ያማረውን ሽቶ ዕጣን ለማጠን፥ የተቀደሰውንም ኅብስት ለማኖር፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በጥዋትና በማታ በሰንበታቱም በመባቻዎቹም በአምላካችንም በጌታ በዓላት ለማቅረብ ለአምላኬ ለጌታ ስም ቤት ልሠራለትና ልቀድስለት አሰብሁ።
ሙሴም እንዳዘዘ እንደ ሥርዓታቸው ዘወትር በየቀኑ፥ በየሰንበታቱም፥ በየመባቻዎቹም፥ በየተወሰኑትም በዓላት፥ በየዓመቱ ሦስት ጊዜ በየቂጣው በዓልና በየሰባቱ ሱባዔ በዓል በየዳሱም በዓል ቁርባን ያቀርቡ ነበር።
ከንቱውን መባ አታቅርቡ፤ ዕጣናችሁን እጸየፋለሁ፤ የወር መባቻ በዓላችሁን፤ ሰንበቶቻችሁን፤ ጉባኤያችሁንና በክፋት የተሞላውን ስብሰባችሁን መታገሥ አልቻልሁም።
እንዲህም በላቸው፦ ‘ለጌታ በእሳት የምታቀርቡት ቁርባን ይህ ነው፤ ለዘወትር ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ዕለት ዕለት ታቀርባላችሁ።
“በሰንበትም ቀን ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥ ለእህልም ቁርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት፥ የመጠጡንም ቁርባን ታቀርባላችሁ።
እንዲሁም ከሚያስተሰርየው ከኃጢአት መሥዋዕት፥ ዘወትርም ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቁርባን፥ ከመጠጥ ቁርባናቸውም ሌላ ለኃጢአት መሥዋዕት ደግሞ አንድ አውራ ፍየል አቅርቡ።።
በወሩ መባቻ ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቁርባን፥ ዘወትርም ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቁርባን፥ ከመጠጡም ቁርባን ሌላ፥ እንደ ሕጋቸው ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርቡ ናቸው።