La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 22:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በለዓምም ባላቅን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፥ ወደ አንተ መጥቼአለሁ፤ በውኑ እኔ አሁን አንዳችን ነገር ለመናገር እችላለሁን? እግዚአብሔር በአፌ የሚያድርገውን ቃል እርሱን እናገራለሁ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በለዓምም፣ “ይኸው አሁን መጥቻለሁ፤ ግን እንዲያው ማንኛውንም ነገር መናገር እችላለሁን? እኔ መናገር የሚገባኝ እግዚአብሔር በአፌ ያስቀመጠውን ብቻ ነው” ብሎ መለሰለት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በለዓምም “ያም ሆነ ይህ አሁን መጥቼ የለምን? ታዲያ አሁንስ ቢሆን በራሴ ምን ኀይል አለኝ? እኔ ልናገር የምችለው እግዚአብሔር የሚነግረኝን ብቻ ነው” ሲል መለሰለት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን፥ “እነሆ፥ ወደ አንተ መጥ​ቼ​አ​ለሁ፤ አሁን አን​ዳ​ችን ነገር ለመ​ና​ገር እች​ላ​ለ​ሁን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአፌ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ቃል እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በለዓምም ባላቅን፦ እነሆ፥ ወደ አንተ መጥቼአለሁ፤ በውኑ አሁን አንዳችን ነገር እናገር ዘንድ እችላለሁን? እግዚአብሔር በአፌ የሚያድርገውን ቃል እርሱን እናገራለሁ አለው።

Ver Capítulo



ዘኍል 22:38
16 Referencias Cruzadas  

ሚክያስ ግን “ጌታ የሚገልጥልኝን ቃል ብቻ እንደምናገር በሕያው ጌታ ስም እምላለሁ!” ሲል መለሰለት።


አክዓብ ግን “አንተ በጌታ ስም የትንቢትን ቃል ስትነግረኝ እውነቱን ግለጥ! ይህንንስ ስንት ጊዜ እነግርሃለሁ?” አለው።


ሚክያስም፦ “በሕያው ጌታ እምላለሁ! አምላኬ የሚለውን እርሱን እናገራለሁ” አለ።


ጌታ የአሕዛብን ምክር ያጠፋል፥ የአሕዛብንም አሳብ ይመልሳል።


የምድር ትሑታንን ያድን ዘንድ እግዚአብሔር ለፍርድ በተነሣ ጊዜ።


በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ፥ የጌታ ምክር ግን እርሱ ይጸናል።


የሐሰተኞችን ምልክት ከንቱ አደርጋለሁ፥ ምዋርተኞችንም አሳብዳለሁ፥ ጥበበኞቹንም ወደ ኋላ እመልሳለሁ፥ እውቀታቸውንም ስንፍና አደርጋለሁ፤


በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እነግራለሁ፤ “ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ” እላለሁ።


ምናልባትም መጠቀም ትችዪ ወይም ታስደነግጪ እንደሆነ፥ ከአስማቶችሽና ከሕፃንነትሽ ጀምረሽ ከደከምሽበት ከመተቶችሽ ብዛት ጋር ቁሚ።


በለዓምም መልሶ የባላቅን ባርያዎች እንዲህ አላቸው፦ “ባላቅ በቤቱ የሞላውን ወርቅና ብር ቢሰጠኝ፥ ትንሹን ወይም ትልቁን ነገር በመፈጸም የአምላኬን የጌታን ቃል ለመተላለፍ አልችልም፤


ባላቅም በለዓምን እንዲህ አለው፦ “በውኑ አንተን ለመጥራት አላክሁብህምን? ለምንስ ወደ እኔ አልመጣህም? በውኑ አንተን ለማክበር እኔ አልችልምን?”


በለዓምም ከባላቅ ጋር ሄደ፥ ወደ ቂርያት ሐጾትም መጡ።


እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “ዛሬ ሌሊት በዚህ እደሩ፥ ጌታም እንደሚነግረኝ እመልስላችኋለሁ”፤ የሞዓብም አለቆች በበለዓም ዘንድ ተቀመጡ።


ጌታም በለዓምን አገኘው፥ ቃልንም በአፉ አድርጎ፦ “ወደ ባላቅ ተመለስ፥ እንዲህም ተናገር” አለው።


በለዓምም መልሶ ባላቅን፦ “ ‘ጌታ የተናገረውን ሁሉ አደርጋለሁ’ ብዬ ነግሬህ አልነበረምን?” አለው።


‘ባላቅ በቤቱ የሞላውን ብርና ወርቅ ቢሰጠኝ፥ በራሴ ፈቃድ መልካምን ወይም ክፉን ነገር ለማድረግ የጌታን ቃል መተላለፍ አልችልም፤ ጌታ የተናገረውን እርሱን እናገራለሁ።’