Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 22:38 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 በለዓምም፣ “ይኸው አሁን መጥቻለሁ፤ ግን እንዲያው ማንኛውንም ነገር መናገር እችላለሁን? እኔ መናገር የሚገባኝ እግዚአብሔር በአፌ ያስቀመጠውን ብቻ ነው” ብሎ መለሰለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 በለዓምም ባላቅን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፥ ወደ አንተ መጥቼአለሁ፤ በውኑ እኔ አሁን አንዳችን ነገር ለመናገር እችላለሁን? እግዚአብሔር በአፌ የሚያድርገውን ቃል እርሱን እናገራለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 በለዓምም “ያም ሆነ ይህ አሁን መጥቼ የለምን? ታዲያ አሁንስ ቢሆን በራሴ ምን ኀይል አለኝ? እኔ ልናገር የምችለው እግዚአብሔር የሚነግረኝን ብቻ ነው” ሲል መለሰለት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን፥ “እነሆ፥ ወደ አንተ መጥ​ቼ​አ​ለሁ፤ አሁን አን​ዳ​ችን ነገር ለመ​ና​ገር እች​ላ​ለ​ሁን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአፌ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ቃል እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 በለዓምም ባላቅን፦ እነሆ፥ ወደ አንተ መጥቼአለሁ፤ በውኑ አሁን አንዳችን ነገር እናገር ዘንድ እችላለሁን? እግዚአብሔር በአፌ የሚያድርገውን ቃል እርሱን እናገራለሁ አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 22:38
16 Referencias Cruzadas  

በሰው ልብ ብዙ ሐሳብ አለ፤ የሚፈጸመው ግን የእግዚአብሔር ሐሳብ ነው።


በለዓም ግን እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “ሌላው ይቅርና ባላቅ በብርና በወርቅ የተሞላ ቤተ መንግሥቱን ቢሰጠኝ እንኳ፣ የአምላኬን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጣስ ከዚያ ያለፈ ወይም ያነሰ ማንኛውንም ነገር ማድረግ አልችልም።


በለዓምም፣ “እግዚአብሔር የሚለኝን ሁሉ ማድረግ እንዳለብኝ አልነገርሁህምን?” ሲል መለሰለት።


እግዚአብሔር በለዓምን ተገናኘው፤ በአፉም መልእክት አስቀምጦ፣ “ወደ ባላቅ ተመለስና ይህን መልእክት ንገረው” አለው።


“በይ እንግዲህ፣ ከልጅነትሽ ጀምሮ የደከምሽባቸውን፣ አስማቶችሽን፣ ብዙ መተቶችን ቀጥዪባቸው፤ ምናልባት ይሳካልሽ፣ ምናልባትም ጠላቶችሽን ታሸብሪባቸው ይሆናል።


የመጨረሻውን ከመጀመሪያው፣ ገና የሚመጣውንም ከጥንቱ ተናግሬአለሁ፤ ‘ምክሬ የጸና ነው፤ ደስ የሚያሠኘኝንም ሁሉ አደርጋለሁ’ እላለሁ።


የሐሰተኞችን ነቢያት ምልክቶች አከሽፋለሁ፤ ሟርተኞችን አነሆልላለሁ፤ የጥበበኞችን ጥበብ እገለባብጣለሁ፤ ዕውቀታቸውንም ከንቱ አደርጋለሁ።


ሰውን ብትቈጣ እንኳ ለክብርህ ይሆናል፤ ከቍጣ የተረፉትንም ትገታቸዋለህ።


እግዚአብሔር የሕዝቦችን ምክክር ከንቱ ያደርጋል፤ የሕዝብንም ዕቅድ ያጨናግፋል።


ሚክያስ ግን፣ “ሕያው እግዚአብሔርን! አምላኬ የሚለውን ብቻ እነግረዋለሁ” አለ።


ሚክያስ ግን፣ “ሕያው እግዚአብሔርን! እግዚአብሔር የነገረኝን ብቻ እነግረዋለሁ” አለ።


‘ሌላው ይቅርና ባላቅ በብርና በወርቅ የተሞላ ቤተ መንግሥቱን ቢሰጠኝ እንኳ፣ እግዚአብሔር የሚለውን ብቻ ከመናገር በቀር ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ውጭ በራሴ ሐሳብ በጎም ሆነ ክፉ ማድረግ አልችልም።’


ባላቅ በለዓምን፣ “በቶሎ እንድትመጣ ልኬብህ አልነበረምን? ለምን አልመጣህም? በርግጥ ወሮታህን ልከፍል የማልችል ሆኜ ነውን?” አለው።


ከዚያም በለዓም ከባላቅ ጋራ ወደ ቂርያት ሐጾት ሄደ።


በለዓምም፣ “እግዚአብሔር የሚሰጠኝን መልስ አመጣላችኋለሁና የዛሬን ሌሊት እዚሁ ዕደሩ” አላቸው። ስለዚህም የሞዓብ አለቆች ከርሱ ዘንድ ቈዩ።


ንጉሡም፣ “ከእውነት በቀር ምንም ነገር በእግዚአብሔር ስም እንዳትነግረኝ የማምልህ ስንት ጊዜ ነው?” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios