La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 18:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የተመረጠውንም ከእርሱ ባቀረባችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኃጢአትን አትሸከሙም፤ እንዳትሞቱም የእስራኤልን ልጆች የተቀደሱ ነገሮች አታረክሱም።’ ”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የተመረጠውን ክፍል ካቀረባችሁ በዚህ በደለኞች አትሆኑም፤ ደግሞም የተቀደሰውን የእስራኤላውያንን መባ አታረክሱም፤ አትሞቱምም።’ ”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ምርጥ የሆነውን ነገር ለእግዚአብሔር ካቀረባችሁ በኋላ በምትመገቡበት ጊዜ በደል አይኖርባችሁም፤ ነገር ግን ምርጥ የሆነው ነገር ከእርሱ ላይ ሳይነሣ ከስጦታው በመመገብ የእስራኤላውያንን የተቀደሰ ስጦታ እንዳታስነውሩ ተጠንቀቁ፤ ይህን ብታደርጉ ግን ትሞታላችሁ።’ ”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ው​ንም ከእ​ርሱ ባነ​ሣ​ችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኀጢ​አት አይ​ሆ​ን​ባ​ች​ሁም፤ እን​ዳ​ት​ሞ​ቱም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የቀ​ደ​ሱ​ትን አታ​ር​ክሱ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የተመረጠውንም ከእርሱ ባነሣችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኃጢአትን አትሸከሙም፤ እንዳትሞቱም የእስራኤል ልጆች የቀደሱትን አታረክሱም።

Ver Capítulo



ዘኍል 18:32
10 Referencias Cruzadas  

ኃጢአት እንዳይሆንባቸውና እንዳይሞቱ፥ ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገቡ ወይም በመቅደሱ ሊያገለግሉ ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ በአሮንና በልጆቹ ላይ ይሆናሉ፤ ለእርሱና ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል።


እርሱንም የሚበላ ማናቸውም ሰው ለጌታ የተቀደሰውን ነገር አርክሶአልና በደሉን ይሸከማል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጠፋል።


“የተቀደሰውንም ስሜን እንዳያረክሱ፥ የእስራኤል ልጆች ለእኔ ከሚቀድሱአቸው ከቅዱሳን ነገሮች ራሳቸውን እንዲለዩ ለአሮንና ለልጆቹ ተናገር፤ እኔ ጌታ ነኝ።


“በመሠዊያዬ ላይ የረከሰ ምግብ ታቀርባላችሁ።” እናንተም፦ “ያረከስንህ እንዴት ነው?” ትላላችሁ። “የጌታ ገበታ የተናቀ ነው” በማለታችሁ ነው።


ከዚህም በኋላ ኃጢአትን እንዳይሸከሙ እንዳይሞቱም፥ የእስራኤል ልጆች ወደ መገናኛው ድንኳን አይቅረቡ።


እናንተም ቤተ ሰቦቻችሁም፥ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያገለገላችሁበት የድካማችሁ ዋጋ ነውና በሁሉ ስፍራ ትበሉታላችሁ።


ጌታም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦


ስለዚህ ያልተገባ ሆኖ ሳለ ይህን ኅብስት የበላ ወይም የጌታን ጽዋ የጠጣ ሁሉ የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ አለበት።


ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላል፤ ይጠጣልም።